ደቡብ ሱዳን የሞለኪውላር ምርመራ ልትጀምር ነው

108
ኢዜአ፤ ጥቅምት 10/2012 ደቡብ ሱዳን የኢቦላ ቫይረስን፣ ቢጫ ወባን፣ የማርበርግ ቫይረስን እና  የስምጥ ሸለቆ ትኩሳት ተላለፊ በሽታዎችን መመርመር የሚያስችል የሞለኪውላር  ምርመራ ሙከራ ልታደርግ መሆኗን ገለጸች፡፡ የሲጂቲኤን ዘገባ እንደሚያሳየው የዓለም ጤና ድርጅት በጁባ ባወጣው መግለጫ “የሞለኪውላር ምርመራ ሙከራው ተግባራዊ መደረጉ በምስራቅ አፍሪካ ሃገራት ለሚከሰቱ ተላላፊ በሽታዎች ወቅታዊና ፈጣን ምላሽ በመስጠት አቅም ለመፍጠር ያስችላል” ማለቱን  ጠቁሟል፡፡ በዓለም ጤና ድርጅት የደቡብ ሱዳን ተወካይ ኦልሻዮ ኦልዮ “ይህ ውሳኔ ለደቡብ ሱዳን በጣም አስደሳችና ትልቅ እርምጃም ነው” ብለዋል፡፡ ይህ የሞለኪውላር ምርመራ ሙከራ መጀመሩ የሀገር ውስጥ አቅም ውስንነትን በመቅረፍ  ለጉንፋን ወረርሽኝ እና ሌሎች ተያያዥነት ያላቸውን ስጋቶችን በመቅረፍ የህዝብን ጤና ለመጠበቅ ያስችላል መባሉንም ዘገባው አክሏል፡፡ የዓለም ጤና ድርጅት መሰል የቤተ-ሙከራ ዘዴዎች እንዲጠናከሩ የላብራቶሪ ስልጠና ለሰራተኞች መስጠቱን እንደሚቀጥልም በዘገባው ተገልጿል፡፡ በደቡብ ሱዳን ለሚገኙት ሞለኩላር ላብራቶሪ የጥራት ደረጃ አስተዳደር ስርዓት ድጋፍ  እየሰጠ እንደሚገኝም  ድርጅቱ አስታውቋል፡፡
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም