በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የሰላም ሽልማት ለዶ/ር አቢይ  አህመድ ተሰጠ

259

ኢዜአ፤ ጥቅምት 9/2012  ለሰላም ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላደረጉ ሰዎች የሚሰጥ  በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነው ሽልማት በሰላም ሚኒስቴር  ለጠቅላይ ሚኒስትር  ዶክተር አቢይ አህመድ  ተሰጥቷል፡፡

የሰላም ቤተሰቦች መከላከያ ሚኒስቴርን ጨምሮ የሰላም ሚኒስቴር ተጠሪ  ተቋማትም  ጠቅላይ ሚኒስትሩን ሸልመዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ  እዚህ  እንዲደርሱ ከጎናቸው በመሆን ላደረጉላቸው ድጋፍ ና  ላበረከቱት አስተዋጽኦ  ለመከላከያ ሚኒስትሩ አቶ ለማ መገርሳ  ዛሬ ከተሰጣቸው ሽልማት የኢትዮጵያ ምልክት ያለውን  ሸልሟቸዋል፡፡

ከዚህ አመት በኋላ የሰላም ሚኒስቴር በየአመቱ ለሰላም አስተዋጽኦ ላበረከቱ ሰዎች እንደሚሸልም በመግለጽ ዛሬ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አቢይ አህመድ በመስጠት ጀምሯል፡፡