“ሰላም መቶ በመቶ ያሸልማል” በሚል መርህ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አቢይ  አህመድ የእውቅና ፕሮግራም ተካሄደ

97
ኢዜአ፤ ጥቅምት 9/2012 “ሰላም መቶ በመቶ ያሸልማል” በሚል መርህ ሐሳብ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አቢይ አህመድ የአለም የሰላም ኖቤል ተሸላሚ በመሆናቸው ና ለሰላም ላበረከቱት አስተዋጽኦ  ሀገር አቀፍ የእውቅና ፕሮግራም በሚሊኒየም አዳራሽ ተካሂዷል፡፡ በእውቅና ፕሮግራሙ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ፣ ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው፣ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሸን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪማሃማት፣ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ፣ አምባሳደሮች፣ ዲፕሎማቶች፣ ከፍተኛ የመንግስት ስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች እና ታዋቂ ግለሰቦች ታድመዋል፡፡ ፕሮግራሙን የሃይማኖት አባቶች በምርቃት በማስጀመር ለጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድና ለኢትዮጵያ ህዝብ እንኳን ደስ አለን ብለዋል፡፡ በዚሁ መርሃ ግብር ላይ ስለ ዶክተር አቢይ አህመድ ስብእና ና እሳቤን የሚያሳይ "አቢይ እንደ ሰው "የሚል ዶክመንተሪም ቀርቧል፡፡
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም