በአረንጓዴ የአሻራ ቀን ችግኝ የተተከለበት የምንዝሮ ቀበሌ አረንጓዴ ፓርክ እንዲሆን ተወሰነ

46
ጥቅምት 9 /2012   በአረንጓዴ የአሻራ ቀን ፕሬዚዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ ችግኝ የተከሉበት የምንዝሮ ቀበሌ አረንጓዴ ፓርክ እንዲሆን መወሰኑን የጎንደር ዙሪያ ወረዳ ግብርና ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡ የጽህፈት ቤቱ ሃላፊ አቶ ባይለየኝ አድማሱ ለኢዜአ እንደተናገሩት ፕሬዚዳንቷ አረንጓዴ አሻራቸውን ባሳረፉበት ቦታ ከተተከሉት ችግኞች መካከል 88 በመቶ የሚሆኑት በተደረገው እንክብካቤ ጸድቀዋል፡፡ በቀበሌዋበ6ነጥብ3ሄክታርየተተከሉትንከ22ሺበላይየሃገርውስጥናየውጭዝርያያላቸውችግኞችየአካባቢው ህብረተሰብበመኮትኮትናበመከባከብየሚጠበቅበትንእያከናወነመሆኑንተናግረዋል። ከህብረተሰቡ እገዛ በተጨማሪም ጽህፈት ቤቱ በቋሚነት በመደባቸው የጥበቃ ሰራተኞች አማካኝነት ከሰውና ከእንስሳት ንክኪ የመጠበቅ ስራ እየተከናወነ መሆኑን ገልፀዋል። የተተከሉት ችግኞች በበጋ ወራት ሊያጋጥም የሚችለውን የእርጥበት ችግር ለማስወገድ የውሃ ማጠራቀሚያ ጋኖችን በመትከል ውሃ የማጠጣት ስራ እንደሚካሄድ ተናግረዋል፡፡ ቀበሌው የአንድ ሀገር መሪ ችግኝ በመትከል አሻራቸውን ያሳረፉበት ታሪካዊ ስፍራ በመሆኑ ከዚህ ዓመት ጀምሮ በአረንጓዴ ፓርክነት እንዲከለል መሰኑን ተናግረዋል፡፡ የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ቀበሌአችን ድረስ መጥተው ችግኝ በመትከላቸው በወቅቱ በደስታ ተቀብለናቸው አብረን ችግኝ ተክለናል ያሉት ደግሞ የምንዝሮ ቀበሌ ነዋሪ አርሶ አደር ማሬ ባዩ ናቸው፡፡ የተተከሉት ችግኞች በቤት እንስሳት ጉዳት እንዳይደርስባቸው በመጠበቅና በመከባከብ ላይ እንደሚገኙ ገልፀዋል፡፡ "ችግኞቹንጠዋትማታበመንከባከብለውጤትእንዲበቃበልማትቡድንተደራጅተንእየሰራንነው"ያሉትደግሞየዚሁቀበሌነዋሪአርሶአደርጋሻውሙጨናቸው፡፡ በወረዳው ሃምሌ 22 ቀን 2011 ዓ.ም በተካሄደው የችግኝ ተከላ ከፕሬዝዳንቷ በተጨማሪ የክልሉ ርእሰ መስተዳድር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ችግኝ በመትከል አሻራቸውን ያሳረፉበት ቦታ ነው። በእለቱ ተካሂዶ በነበረው የአረንጓዴ አሻራ ስነ-ስርአት ላይ ከ1ሺ 500 በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች ችግኞችን  በመትከል አሻራቸውን አኖረዋል፡፡ ከጽህፈት ቤቱ የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው የአረንጓዴ አሻራ ቀን ምክንያት በማደረግ 82 ሄክታር በሚሸፍን ቦታ ላይ የተተከሉ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ችግኞች በህብረተሰቡ ተሳትፎ እንክብካቤ እተደረገላቸው ነው፡፡ በማእከላዊ ጎንደር ዞን በአረንጓዴ አሻራ እለትና በመደበኛው መርሃ ግብር በክረምቱ ወራት የተተከሉ ከ70 ሚሊዮን በላይ ችግኞች በአሁኑ ወቅት በህብረተሰቡ ተሳትፎ እንክብካቤ እየተደረገላቸው መሆኑን ከዞኑ ግብርና መምሪያ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡      
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም