ኦፍላ ወረዳ አውቶቡስ ተገልብጦ የስድስት ሰዎች ህይወት አለፈ

218

ጥቅምት 9/2012 በትግራይ ደቡባዊ ዞን ኦፍላ ወረዳ በደረሰ የተሽከረካሪ አደጋ ስድስት ሰዎች ሲሞቱ 22 ሰዎች ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት የደረሰባቸው መሆኑን ፖሊስ አስታወቀ።

የዞኑ ትራፊክ ፖሊስ ኃላፊ ኮማንደር አብርሃ ወረደ ለኢዜአ እንደገለፁት አደጋው የደረሰው 28 ሰዎችን አሳፍሮ ከኮረም ከተማ ወደ ፋላ ይጓዝ የነበረ የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3- 06938 ትግ የሆነ የህዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ ትላንት ቀትር ላይ ፍቅረ ወልዳ በተባለ ስፈራ በመገልበጡ ነው ።

በአውቶቡሱ ተሳፋሪዎችና  በረዳቱ መካከል በክፍያ በተፈጠረ ጭቅጭቅ አሽከርካሪው አውቶቡሱን አቁሞ ሲወርደ ታኮ ባለማድረጉ 150 ሜትር ጥልቀት ካለው ገደል ተንሸራቶ ገብቷል “ብለዋል።

በአደጋው አንድ የስድስት ወር ህፃንን ጨምሮ ህይታቸው ያለፈ ስድስት ሰዎች አስከሬን ለቤተሰቦቻቸው መሰጠቱን ተናግረዋል ።

ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች በመቀሌ፣ማይጨውና ኮረም ሆስፒታሎች ህክምና እየተደረገላቸው መሆኑን  አስታውቀዋል ።

እንደ ኮማንደር አብርሃ ገለጻ ፖሊስ አሽከርካሪውን በቁጥጥር ስር አውሎ ጉዳዩን እያጣራ ነው ።