ከ50 ሺ በላይ ነዋሪ ተሳታፊ የሚሆንበት የማስ ስፖርት ነገ ይካሄዳል

153

ጥቅምት 8/2012 ከ 50ሺ ሰው በላይ ህዝብ ተሳታፊ የሚሆንበት አምስተኛው ከተማ አቀፍ የማስ ስፖርት መርሃ-ግብር ነገ እሁድ ከማለዳው 12:30 ጀምሮ በመስቀል አደባባይ ይካሄዳል፡፡

ነገ በሚካሄደው የአምስተኛ ዙር የማስ ስፖርት መርሃ-ግብር ላይ ከተለያዩ የስፖርት ማህበራት የተውጣጡ ስፖርተኞች እና የስፖርት ማህበራት ተሳታፊ ይሆናሉ፡፡

የከተማ አስተዳደሩ አካላዊ እንቅስቃሴ ማድረግን ባህል ያደረገ ማህበረሰብ ለመፍጠር እና የማስ ስፖርትን ከኪነ-ጥበብ ጋር በማዋሃድ መርሃ-ግብሩን ወደ ፌስቲቫል ለማሳደግ እየሰራ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

ከ50 ሺ በላይ የሚሆኑ የተለያዩ የከተማዋ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳታፊ በሚሆኑበት በዚህ የአምስተኛው ዙር የማስ ስፖርት መርሃ-ግብር ላይ የከተማችን ነዋሪዎች ተሳታፊ እንዲሆኑ ጥሪ ማቅረቡን የከንቲባ ጽህፈት ቤት በማህበራዊ ገፁ አስነብቧል፡፡