በሳውዲ አረቢያ በደረሰ የመኪና አደጋ የ35 ሰዎች ህይወት አለፈ

71
ኢዜአ፤ ጥቅምት 6/2012 በሳውዲ አረቢያ በደረሰ የመኪና አደጋ 35 ሰዎች ሲሞቱ አራት መቁሰላቸው ተገለፀ በሳውዲ አረብያ መዲና የመንገደኞች አውቶብስ ከጭነት መኪና ባጋጠመው የግጭት አደጋ 35 ሰዎች የሞቱ ሲሆን አራት ሰዎች መቁሰላቸውን የአገሪቱ ፖሊስ ቃል አቀባይ ገልጸዋል፡፡ ቃል-አቀባዩ ለሳውዲ ዜና አገልግሎት እንደገለፁት ከኤስያና አረብ አገራት በመጡት ተጓዦች በኮንትራት የተያዘው የመንገደኞች አውቶብስና ከባድ የጭነት መኪና የግጭት አደጋ የደረሰው አል-አክሃል በምትባል ከተማ ነው፡፡ አደጋው ትላንት ከሰአት በኋላ መካ እና መዲና በሚያገናኝ መንገድ ላይ መድረሱንም  ጨምረው ገልጿል፡፡ በአደጋው ወቅት የመቁሰል አደጋ የደረሰባቸው ሰዎች በአል-ሃምና ሆስፒታል ክትትል እየተደረገላቸው መሆኑን  የሳውዲ ዜና አገልግሎት ከባለስልጣናት አገኘሁ ብሎ ያሰራጨው ዘገባ ያመለክታል፡፡ ምንጭ፡-አልጀዚራ
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም