ሊቢያ 95 ህገ-ወጥ ስደተኞችን ወደ ግብፅ እንዲመለሱ አደረገች

206

ጥቅምት 6/2012 በምስራቅ ቤንጋዚ ከተማ የሊቢያ የስደተኞች ቁጥጥር መምሪያ 95 ህገ-ወጥ ስደተኞችን ወደ ግብፅ መላኳን  ተዘገበ፡፡

መምሪያው እንዳስታወቀው ስደተኞቹ የተመለሱበት ምክንያት በተላላፊ በሽታዎች የተጠቁ መሆናቸው የተገለጸ ሲሆን  በግብፅ ድንበር በኩል በአውቶቡሶች እንዲመለሱ መደረጉን በመረጃው ተጠቅሷል።

በተጨማሪም መምሪያው ከአንድ መቶ በላይ ህገ ወጥ ስደተኞችን ወደ ግብፅ እና ናይጄሪያ እንደመለሰም አስታውቋል።

ዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት ባሳለፊነው ሳምንት መጨረሻ እንዳስታወቀው በሊቢያ ከ 650ሺ  በላይ ሕገ ወጥ ስደተኞች መኖራቸውን የገለፁ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ ሴቶችና ሕፃናትን ጨምሮ 6ሺ  ያህሉ  ማቆያ ማዕከላት ውስጥ እንደሚገኙ ይፋ ማድረጉን በመረጃው ተጠቅሷል፡፡

እ.ኤ.አ በ 2011 የቀድሞው መሪ ሙሐመድ ጋዳፊ ከስልጣን ከተወገደ በኋላ ሀገሪቱ አለመረጋጋት በማጋጠሙ በሺዎች የሚቆጠሩ ህገ-ወጥ ስደተኞች፣ አብዛኛዎቹ አፍሪካውያን ሊቢያን እንደመሻገሪያ በመጠቀም የሜዲትራንያንን ባህር አቋርጠው ወደ አውሮፓ ጉዞ ለማድረግ እንደ አማራጭ እንደሚጠቀሙ በመረጃው ተጠቅሷል።

(ዥንዋ)