የእምቦጭን ጉዳት ለመቀነስ ችግር ማጋጠሙ ተገለጸ

117
  ጥቅምት 5 /2012 በጣና ሃይቅ ላይ የተከሰተው እምቦጭ ለማስወገድ የመጡት ማሽኖች በአግባቡ መስራት ባለመቻላቸው አረሙ እያስከተለ ያለውን ጉዳት ለመቀነስ ችግር ማጋጠሙ ተገለጸ፡ አርሶ አደር ፈንታሁን ውቤ በጎንደር ዙሪያ ወረዳ ሻጎመንጌ ቀበሌ ነዋሪ ሲሆኑ እምቦጭ የተባለው አረም አካባቢያቸው በሚደርሰው የጣና ሀይቅ ሀብትን እየጎዳው መሆኑን ለኢዜአ ተናግረዋል። አሳ በማጥመድ፣ ከሀይቁ ዳር ለከብቶቻቸው የሚሆን ሳር በማጨድና ውሃ በማጠጣት ይጠቀሙበት የነበረው በአረሙ ምክንያት እንዳሳጣቸውም አመልክተዋል። አርሶ አደሩ በጉልበቱ አረሙን ለማጽዳትና ለማስወገድ ቢሞክርም በጊዜ ሂደት ከአቅም በላይ እየሆነ በመምጣቱ ለመንግስት በማሳወቅ ማሽኖች እንደመጣላቸው ገልጸዋል። ሆኖም በአግባቡ ስለማይሰሩ የአረሙን ስርጭት ለመቀነስ አዳጋች ሆኖባቸው መቸገራቸው ተናግረዋል። በጣና ሃይቅ ፕሮጀክት የማሽኖች መካኒክ የሆኑት አቶ መሃመድ ሃሰን በበኩላቸው ሰባት ማሽኖች የእምቦጭ አረምን ለማስወገድ ወደ ስራ መግባታቸውን አስረድተዋል። "ከማሽኖቹ መካከልም አራቱ የእምቦጭ መሰብሰቢያ ቀሪዎቹ ደግሞ የማጓጓዛና አጋዥ ማሽኖች ናቸው"  ያሉን መካኒኩ በነዳጅ አወሳሰዳቸውና የማስወገድ አቅማቸው የተለያየ ባህሪ ያላቸው እንደሆኑ ተናግረዋል። በእምቦጭ ማስወገድ ስራው ሁሉንም ማሽኖች አቀናጅቶ በማሰራት ለውጥ በማምጣት በኩል የመለዋወጫና የባለሙያዎች የአደጋ መከላከያ ቁሳቁሶች ችግር መኖሩን ጠቁመዋል። በዚህም ምክንያት ማሽኖቹ በአግባቡ መስራት ባለመቻላቸው አረሙ እያስከተለ ያለውን ጉዳት ለመቀነስ ችግር ማጋጠሙን ገልጸዋል። በባህርዳር ዩንቨርሲቲ የጣና ፕሮጀክት ቴክኒካል ቡድን አስተባባሪ አቶ ዮናስ ምትኩ እንዳሉት ዩኒቨርሲቲው ከሙላት ኢንዱስትሪያል ኢንጅነሪንግ ጋር በመተባበር የእምቦጭ ማጨጃና ማጓጓዛ ማሽኖችን በሀገር ውስጥ አምርቷል። በዚህም 12 ሜትር ኩብ በአንድ ጊዜ ነቅሎ የሚጭን ማሽን፣ 80 ሜትር ኩብ የመጫን አቅም ያላቸው ሁለት ተንቀሳቃሽና አንድ ከሃይቁ ዳር የተተከለ የመጓጓዛ ማሽኖች በማምረት እምቦጭን የማስወገድ ስራ ላይ ተሰማርተዋል። ማሽኖቹ በስራ እድል ፈጠራ፣ በቴክኖሎጂ ሽግግርና የውጭ ምንዛሬ በማስቀረት ፋይዳቸው የጎላ መሆኑን ጠቁመው በሙሉ አቅማቸው ለማሰራትም በቴክኒክና ሙያ ዘጠኝ ባለሙያዎችን አሰልጥነው ማሰማራታቸውን አመልክተዋል።       "የጣና ጉዳት የራሴ ጉዳት በመሆኑ ከባህርዳር ዩንቨርሲቲ ጋር በመተባበር ከፍተኛ ማሽነሪዎችን በማምረት ችግሩን ለመቅረፍ የበኩሌን እየተዋጣሁ ነው" ያሉት ደግሞ የሙላት ኢንዱስትሪ ኢንጅነሪንግ ስራ አስኪያጅ አቶ ሙላት ባሳዝነው ናቸው።   አሁን ላይ ከባድ ማሽነሪዎች በማይገቡባቸው አካባቢዎች በአርሶ አደሮች ጉልበት የሚካሄደውን የእምቦጭ ማስወገድ ስራ ለማገዝ የሚያስችል በአንድ ሰው የሚንቀሳቀስ አነስኛ ማሽን መስራቱን ገልጿል።   አራተኛው የአቶ ሙላት ንግግር መግቢያ 02 ፡33"  ገበሬዎች ማሽን በማይገባበት---የአካባቢው ሰዎች እያመረተ እንዲጠቅምበት እየሰራን ነው" መውጫ03፡23   በአማራ ክልል የጣና ሃይቅና ሌሎች የውሃ አካላት ጥበቃና ልማት ኤጀንሲ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ዘላለም ልየው "የክልሉ መንግስት ለጣናና ሌሎች ውሃ አካላት ትኩረት በመስጠቱ በቅርቡ መስሪያ ቤታቸውን በኤጀንሲ ደረጃ አቋቁሟል" ብለዋል። ኤጀንሲው ከተቋቋመ ከወር ያልበለጠ ጊዜ ቢኖረውም በተፋሰስ ልማት፣ በመጤ አረም መከላከል፣ በደረቅና ፍሳሽ ቆሻሻ ማስወገድና በብዝሃ ህይወት ጥብቃ ላይ አተኩሮ ለመስራት እየተንቀሳቀሰ ነው። "በጣና ሃይቅ ላይ የተከሰተው እምቦጭ የተባለውን መጤ አረም ያለበትን ሁኔታ ለማወቅ የዳሰሳና ቅኝት ጥናት በማካሄድ መረጃ በመሰባሰብ የመተንተን ስራ እየተሰራ ነው" ብለዋል። በበጀት ዓመቱም በሰው ኃይል 90 በመቶ እና በማሽነሪዎች ደግሞ 20 በመቶ የሚሆነውን እምቦጭ ለማከናወን ታቅዷል። አቶ ዘላለም እንዳሉት በእምቦጭ ማስወገድ ስራውም በጣ ሀይቅ አዋሳኝ ወረዳዎችና ቀበሌዎች ከ80 ሺህ በላይ ህዝብ በማሳተፍ ከሚቀጥለው ወር መግቢያ ጀምሮ የዘመቻ ስራ ለማከናወን ዝግጅት እየተደረገ ነው። በተጨማሪም ሁሉንም ማሽኖች ወደ ስራ ለማስገባት ቴክኒካል ኮሚቴ በማቋቋም ርክክብ እንደሚደረግ ጠቁመው የመለዋወጫ እጥረት ችግር ለመፍታት ከሀገር ውስጥ አምራች ድርጅቶች ጋር በቅርበት እንደሚሰራ አስረድተዋል። አምስተኛው የአቶ ዘላለም ንግግር መግቢያ03 ፡37 "ያም ሆነ ይህ ማሽኖችን---ቴክኒካል ኮሚቴ የግድ ያስፈልጋል" መውጫ 04 ፡34 የክልል እና ፌደራል ባለድርሻ አካላት የተፈጥሮ ሃብቱን ለመጠበቅ ተባብረው በጋራ እንዲሰሩም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።      
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም