ኬንያ ከአፍረካ ሀገራት በለጋስነት ቀዳሚ ሆነች

258

ጥቅምት 5/2012 ኬንያ በለጋስነት ከአለማችን 11ኛ ደረጃን ስትይዝ ከአፍሪካ ደሞ የመጀመሪያውን ይዛለች ተባለ፡፡

ከተቀመጠው  መመዘኛ 47 በመቶ በማምጣት እንደሆነም አዲሱ ጥናት አመልክቷል ፡፡

‘ቻሪቲ ኤድ ፋውንዴሽን’ /Charities Aid Foundation/ የተባለ ተቋም ለ10ኛ ጊዜ የአለም የለጋሾች መመዘኛ ላይ ባወጣው ሪፖርት እንዳስታወቀው ከግማሽ በላይ ኬንያውያን ለበጎ አድራጎት ድርጅቶች ገንዘብ ያዋጣሉ፡፡

ድርጅቱ ባለፉት አስርት አመታት ግዜያቸውንና ገንዘባቸውን ለበጎ ተግባራት የሚያውሉ ሀገራትን ለመመዘን በ125 ሀገራት ባደረገው ጥናት ነው ኬንያ ከአፍሪካ የመጀመሪያ የሆነችው፡፡

የቻሪቲ ኤይድ ፋውንዴሽን ከፍተኛ ባለሞያ ጆን ሎው እንዳሉት ጥናቱ የተደረገው ከ2009 እስከ 2018 እ.ኤ.አ ሲሆን፤ ከ125 ሀገራት በተለዩ 1 ነጥብ 3 ሚሊዮን ሰዎች ላይ ነው፡፡

በማደግ ላይ ካሉ ሀገራት ኬንያ ኢንዶኔዠያን ተከትላ ሁለተኛ ደረጃን ስትይዝ ሲንጋፖር በሶስተኛነት ተከትላለች፡፡

ባለፉት አስርት አመታት በኬንያ ከሀገሪቱ ህዝብ ከግማሽ በላይ ለበጎ እድራጎት ግዜና ገንዘባቸውን ሲለግሱ  አብዛኛዎቹ ኢንዶኔዥያውንም ከምንግዜውም በላይ ለጋስነታቸው ጨምሯል ፡፡

በአስር አመት ውስጥ በተሰራው ጥናት ከአለማችን ለጋስ ሀገራት በ58 በመቶ አሜሪካ የመጀመሪያውን ደረጃ ስትይዝ  በ57 በመቶ  ኒውዝላንድ ሁለተኛ  ፣አየር ላንድ በ56 በመቶ ሶስተኝነት ተቀምጠዋል፡፡

ጥናቱ አክሎም በእንግዳ ተቀባይነት ወንዶች በ49 በመቶ  ሴቶች በ46 በመቶ እንግዳ ተቀባይ ናቸው ያለው ሲሆን፤ በገንዘብ ልገሳ ግን   በ29  በመቶ  በእኩል ደረጃ  ተጠቅሰዋል፡፡

የተቸገሩ ሰዎችን በመርዳት ወንዶች ከሴቶች የተሻሉ ናቸውም ተብሏል፡፡

በአለማችን የልግስና ባህል እያደገ ከመምጣቱ ጋር በተገናኘ በደረጃ ከተቀመጡት ግማሹ ከኢስያ፣ሶስቱ ከአፍሪካ እንዲሁም አንድ ከአውሮፓና አንድ ከአሜሪካ ሀገራት መሆናቸው  ለጋስነት  የሁሉም ባህልና ሀይማኖት መገለጫ ነው ብሎታል  ጥናቱ ፡፡(ሲ.ጂ.ቲ.ኤን)