ወልድያ እግር ኳስ ክለብን በአዲስ መልክ ለማጠናከር እየተሰራ ነው- የከተማው ከንቲባ

207

ወልድያ ጥቅምት 4/ 2012  …… የወልድያ ከነማ እግር ኳስ ክለብን ህዝባዊ  መሰረት ለማስያዝና ወደ ቀድሞው ዝናው ለመመለስ እየተሰራ መሆኑን የከተማው አስተዳደር ከንቲባ አስታወቁ ።

የክለቡ ስራ አስኪያጅ አቶ እሸቱ አባተ በገዛ ፍቃዳቸው ኃላፊነታቸውን እንደሚለቁ ይፋ አድርገዋል ።

የከተማ ው ከንቲባ አቶ መሀመድ ያሲን በመድረኩ ላይ እንደገለፁት ክለቡን በአዲስ መልክ በማዋቀር በ2013 ዓም ወደ ፕሪሚየር ሊጉ እንዲመለስ ተገቢውን ጥረት ሁሉ ይደረጋል ብለዋል ።

የክለቡን የተጓደሉ የቦርድ አመራሮች የመተካት፣ የደጋፊ ማህበር አመራሮችን የመምረጥ፣የተጫዋቾችን ደመወዝና ጥቅማ ጥቅም የመወሰንና የተጫዋቾች ግዥና ዝውውር የመፈፀም ስራዎች እየተከናወኑ መሆናቸውን ተናግረዋል ።

የእግር ኳስ ክለቡ ዋና አሰልጣኝ በማድረግ አቶ ንጉሤ ኃይሉ መቀጠሩንም ከንቲባው ይፋ አድርገዋል ።

“አዲስ ኃይል ቢተካ ክለቡ ካጋጠመው ችግር ፈጥኖ በመውጣት ለውጤት ያበቃል የሚል እምነት ሰላለኝ በፍቃደኝነቴ ኃላፊነቴን ለመልቀቅ ወሰኛለሁ “ ሲሉም ለመልቀቅ መዘጋጀታቸውን ይፋ አድርገዋል ።