በትግራይ የሰንደቅ ዓላማ ቀን ዛሬ በድምቀት ተከብሯል

93
ጥቅምት 3/2012/ መቐለ /ኢዜአ/ ..... የትግራይ ህዝብ አንድነቱንና ሰላሙን ጠብቆ የጀመረውን ፀረ ድህነትና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን የማቃለል ትግል አጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ የክልሉ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አሳሰቡ ። የትግራይ  ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ምክርቤት አፈ ጉባኤ አቶ ሩፋኤል ሽፋረ የሰንደቅ ዓላማ ቀኑን በመቀሌ ስታዲዮም ዛሬ በድምቀት ሲከበር እንደተናገሩት  የትግራይ ህዝብ  አንድነቱና  ሰላሙን  ጠብቆ የጀመረውን የፀረ ድህነት ትግል  እንዲያጠናክር አሳስበዋል። ላለፉት 12 አመታት የተከበረው የሰንደቅ አላማ  ቀን የብሄሮች፣ ብሄሮችሰቦችና ህዘቦች አንድነት በማጠናከር ትልቅ ሚና ተጫውቷል በማለት ገልፀዋል። የዘንድሮ የሰንደቅ አላማ ቀን ስናከበር የተጀመሩ  የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለማስወገድ  ትግላችን አጠናክረን  ለመቀጠል ቃል በመግባት ነው ብለዋል። ባለፉት አመታት የተከበሩ ተመሳሳይ በዓላት የኢትዮጰያ ብሄሮች፣ብሄረሰቦችና ህዝቦች ለልማት እንዲነሳሱ አስተዋፅኦው ትልቅ እንደነበረም አስታውሰዋል አፈጉባኤው። በሰንደቅ አለማ  ላይ እተፈፀሙ ያሉ ጥሰቶች ለመከላከል ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣም አቶ ሩፋኤል ጥሪ አቅርበዋል። በሰንደቅ አላማው በዓል ላይ የተገኙ የበአሉ ተሳታፊዎች በበኩላቸው ሰንደቅ አላማችንን  ከፍ ብሎ እንዲውለበለብ ብዙ መስዋእትነት የተከፈለ በመሆኑ ልናከብረውና ልንንከባከበው ይገባል ሲሉ ተናግሯዋል። በበአሉ ላይ ከተሳተፉት መካከል የመቀሌ ከተማ ነዋሪ ወይዘሮ ትብለፅ ሓጎስ እንዳሉት የበአሉ መከበር የትግራይ ህዝብ ሰላምና አንድነት  ለማጠናከር ጉልህ ሚና ይኖረዋል ። በክልሉ የተረጋጋ ሰላም በመኖሩ የሰንደቅ አላማ ቀን እያከበርን እንገኛለን ያሉት ወይዘሮ ትብለፅ የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ እንዲከበር ሁሉም ኢትዮጵያዊያን ተባብረው ሊሰሩ  ይገባል ብለዋል ። ሰንደቅ አላማችን ኢትዮጵያውያን ለነፃነታቸው ሲሉ መስዋእትነት የከፈሉበት የሰላም ምልክት በመሆና  መንከባከብና ማክበር ግድ ይላል ያሉት ደግሞ ተጋዳላይ ብርሃኑ ፀጋይ  ናቸው። አሁን እየተከበረ ያለው የሰንደቅ አላማ ቀን ድህነትን ለማሸነፍ በሙሉ አቅማችን ተሰልፈን እየሰራን ባለንበት ወቅት በመሆኑ ትግላችን ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉም ገልፀዋል። ኢትዮጵያውያን  ከብሄር ተኮር ጥቃት ወጥተን አንድነታችን በማጠናከር የአገሪቱ  ህልውና ለማስቀጠል በአንድነት ልንሰራ ይገባልም ብለዋል  ። የሰንደቅ አላማ ቀን ሲከበር ልማትን እያረጋገጥን መሆን አለበት ያሉት ደግሞ ሌላዋ የበአሉ ተሳታፊ ወይዘሮ ምሕረት ገብረእግዝአብሄር ናቸው።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም