የደቡብ ክልል ምክር ቤት አስረኛ መደበኛ ጉባኤ ነገ ይጀመራል

62
ሀዋሳ ኢዜአ ጥቅምት 3/2012 የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሀዝቦች ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት አምስተኛ ዓመት አስረኛ መደበኛ ጉባኤ ከነገ ጀምሮ ለአራት ቀናት እንደሚያካሂድ ምክር ቤቱ አስታወቀ። ምክር ቤቱ በቆይታው የዘጠነኛ መደበኛ ጉባኤ ቃለ ጉባኤን ፣ የክልሉ መንግስት የ2011 ዓ.ም. የዕቅድ አፈጻጸምና  የተያዘው የስራ ዘመን ዕቅድ ዙሪያ በመወያየት እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል። ጉባኤው የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዋና ኦዲተር አፈጻጸምና ዕቅድን ይገመግማል። የምክር ቤቱ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዛሬ ለኢዜአ እንደገለጸው ጉባኤው ልዩ ልዩ አዋጆችንና ደንቦችን መርምሮ ያጸድቃል፤ የተለያዩ ሹመቶችን እንደሚሰጥ ይጠበቃል።  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም