በሞቃዲሾ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ቅጥር ግቢ በደረሰ ፍንዳታ በርካቶች ቆሰሉ

89
ኢዜአ ጥቅምት 3/2012 በሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ  በሶማሊያ የተባበሩት መንግስታት የእርዳታ ተልእኮ እና በሶማሊያ የአፍሪካ ህብረት ተልእኮ ግቢ ውስጥ በደረሰ ፍንዳታ  ብዙ ሰዎች መቁሰላቸውን ዥንዋ ዘገበ፡፡ በአፍሪካ ቀንድ ውስጥ ለእንደዚህ አይነቱ  የጥፋት ድርጊቶች ምክንያት የለሽና አሳፋሪ መሆናቸውን በሶማሊያ የተባበሩት መንግስታት ዋና ፀሃፊ ልዩ ተወካይ ጄምስ ስዋን ተናግረዋል፡፡ በሰብአዊነት፣ በሰላም ግንባታ እና በልማት ጉዳዮች ላይ ከሶማሊያ ህዝብ ጋር አብረው የሚሰሩ ሠራተኞቻችን ላይ ይህ  ግልጽ የሆነ የሽብርተኝነት ተግባር መፈፀሙ አሳዝኖኛል ሲሉ ሰዋን መናገራችወን መረጃው አትቷል። ፍንዳታው የተከሰተው በተባበሩት መንግስታት እና በሶማሊያ የአፍሪካ ህብረት ተልእኮ  ተቋማት በሚገኙበት  ግቢ ውስጥ ሲሆን በፍንዳታውም በርካታ ስዎች እንደቆሰሉ በመረጃው ተጠቅሷል። “አብዛኛዎቹ ሰራተኞቻችን የከፋ ጉዳት አላጋጠማቸውም፤ የቆሰሉ የስራ ባልደረቦቻችን ከደረሰባቸው ጉዳት ሙሉ በሙሉ እንዲያገግሙ  እንሻለን” ሲሉ ስዋን አክለው ተናግረዋል፡፡ ከአልቃይዳ ጋር ግንኙነት ያለው  የአልሸባብ ታጣቂ ቡድን ለጥቃቱ ሃላፊነቱን እንደወሰደ ዥንዋ ዘግቧል፡፡    
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም