ሽልማቱ ሀገራዊ ለውጡን ከዳር ለማድረስ ተነሳሽነትን እንደሚያጎለብት የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር ፕሬዚዳንት ገለጹ

185
ጥቅምት2/2012ጠቅላይ ሚስትር ዶክተር አብይ አህመድ የኖቤል የሰላም ተሸላሚ መሆናቸው የተጀመረውን ሀገራዊ ለውጥ ከዳር ለማድረስ ተነሳኝነትን እንደሚያጎልበት የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር ፕሬዚዳንት ገለጹ፡፡ የማህበሩ  ፕሬዚደንት ዶክተር ዮሐንስ በንቲ ለኢዜአ እንዳሉት ጠቅላይ ሚስትሩ ያገኙት ዓለም አቀፍ ሽልማት የሀገሪቱ ህዝቦች በየተሰማሩት የስራ ዘርፍ በርትተው በመስራት የለውጡን ዘላቂነት ለማረጋገጥ ይበልጥ ያነሳሳል። የመምራን ማህበሩም በመማር ማስተማር ስራ መላ አባላቱን በማሳተፍ የትምህርት ጥራትን በማስጠበቅና ሰላማዊ የማስማር ሂደት እንዲጠናከር የጠቅላይ ሚነስትሩን አርአያነት ወደታች በማውረድ እንደሚሰራ ተናግረዋል። "ይህም ለሃገር ማህበራዊ፣ ምጣኔ ሀብታዊና ፖለቲካዊ እምርታ ቁልፍ የሆነውን የሰው ኃይል በእውቀት ክህሎትና ስነ ምግባር አንጾ ለማውጣት የመምራኑን ተነሳሽነት ይፈጥራል" ብለዋል። የማህበሩ  ፕሬዚደንት  ሽልማቱ ሀገራዊ ለውጡን ከዳር ለማድረስ ተነሳሽነትን  እንደሚያጎለብት ገልጸው  "ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የዓለም አቀፍ የኖቬል ተሸላሚ በመሆነዎ እንኳን ደስ ያለዎት" በማለትም የደስታ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም