በጋምቤላ ከተማ 38 ክላሽንኮቭ ጠመንጃዎችና ተጠርጣሪዎች ተያዙ

99
ጋምቤላ  ጥቅምት 2 ቀን 2012 ከጋምቤላ ከተማ 38 ክላሽንኮቭ ጠመንጃዎች ከሁለት ተጠርጣሪዎች ጋር ዛሬ በቁጥጥር ሥር ዋሉ። የክልሉ የሰላምና ጸጥታ ጉዳዮች ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ አቶው አኮት እንደገለጹት መሣሪያዎቹ ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ሥር የዋሉት በክልሉ ጸጥታ ኃይል፣ ፌዴራል ፖሊስና መከላከያ ሠራዊት ለሦስት ቀናት ባደረጉት የተቀናጀ ጥረት ነው። የጦር መሣሪያዎቹና ተጠርጣሪዎቹ የተያዙት  ከአንድ ግለሰብ ቤት ኮድ 3 ሠሌዳ ቁጥር ቁጥር አዲስ አበባ 55966 በሆነ የጭነት ተሽከርካሪ ጋር ነው። በክልሉ እየተስፋፋ ያለውን ሕገ ወጥ የጦር መሣሪያዎች ዝውውር ለመግታት የክልሉና የፌዴራል ጸጥታ አካላት ጋር ተቀናጅተው በመሥራት ላይ  መሆናቸውን ገልጸዋል። የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽነር ኡቲያንግ ኡቻን እንተናገሩት ክልሉ ድንበር ያለው ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ሕገ ወጥ የጦር መሣሪያዎች ዝውውር መበራከቱን ተናግረዋል። ችግርን ለመካለካል በሚደረገው ጥረት ሕዝቡና  ጸጥታ አካላት ለሚያደርጉት ጥረት አመስግነው፣ በቀጣይም ቁጥጥሩ ይጠናከራል ብለዋል።  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም