በቱኒዚያ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ እየተካሄደ ነው

368

ኢዜአ ጥቅምት2/2012 ቱኒዚያኖች አዲስ ፕሬዝዳንት ለመምረጥ ድምፅ እየሰጡ ነው ፤በመጨረሻው ዙር ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ወደ ፖለቲካው አዲስ የገቡ ተፎካካሪዎች ናቸውም ተብሏል፡፡

የንግድ ሰው የሆኑት ካቢል ካሩይ እና በጡረታ የተገለሉት የቀለም ሰው ካኢስ ሰይድ ለፕሬዝዳንትነት እየተወዳደሩ መሆኑን ቢቢሲ አስነብቧል፡፡

የ56 አመቱ ሚስተር ካሩይ በህገወጥ የገንዘብ ዝውውርና በታክስ ማጭበርበር ተከሰው እስርቤት የቆዩ ሲሆን የምርጫ ቅስቀሳው እዛው ባሉበት ሲያካሄዱ ነበር ፤ሆኖም የቀረበባበቸውን ክስ አልተቀበሉትም ፡፡

እጩው ፕሬዝዳንት ካሩይ ከአራት ቀናት በፊት ከእስር የተለቀቁ ሰሆን በመጀመሪያ ዙር ምርጫ 15.6 ከመቶ በማግኘት በሁለተኝነት አጠናቀዋል፣ሚስተር ሰይድ በበኩላቸው 18.4በመቶ አግኝተዋል፡፡

የቱኒዚያ የምርጫ ኮሚሽን እንዳለው ሚስተር ካይሮ እየተካሄደ ባለው ምርጫ ካላሸነፉ በምርጫ ቅስቀሳው በሚዛናዊነት አልተሳተፍኩም ሊሉ እንደሚችሉ ገልጿል፡፡

ሁለቱ እጩዎች በመጀመሪያው ዙር ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ 24 እጩዎችን በማሸነፍ የቱኒዚያ የፖለቲካ መሰረት እንደቀየሩ ዘገባው አውስቷል፡፡

የሃገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር የሱፍ ቻሄድ እና የቀድሞው የሓገሪቱ የሽግግር ፕሬዝዳንት ሞንሲፍ ማርዙኪ በእጩነት መቀጠል እንዳልቻሉ የተገለፀ ሲሆን መራጮች በሃገሪቱ በተቀዛቀዘው ኢኮኖሚ፣ከፍተኛ ስራ አጥነትና ደካማ የመንግስት አገልግሎት ድምፅ እንደነሷቸው ታውቋል፡፡