ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ዛሬ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ ይሰጣሉ

5239

አዲስ አበባ ሰኔ 11/2010 ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ዛሬ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ ይሰጣሉ ተባለ።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ  ከሰዓት በኋላ ከቀኑ 8፡00 ጀምሮ 4ኛ ልዩ ስብሰባውን ያካሂዳል።

በዚሁ ልዩ ስብሰባ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ተገኝተው በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ገለፃ የሚያደርጉ ሲሆን ከምክር ቤቱ አባላት ለሚነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽ ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።