በኦሮሚያ የተለያዩ ከተሞች የድጋፍ ስልፎች እየተካሄዱ ነው

423
ጥቅምት 2/2012 ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ  አህመድ ባገኙት የኖቤል ሰላም ሽልማት የተሰማቸው ደስታ በመግለጽ በኦሮሚያ የተለያዩ ከተሞች የድጋፍ ስልፎች እየተካሄዱ ነው
አምቦ፣ ፍቼ፣ መቱ፣ ቡኖ በደሌ ፣ ነገሌ፣  ጅማ እና በሌሎችም የኦሮሚያ ከተሞች የድጋፉ ሰልፉ እየተካሄደ ይገኛል።

በተለይ በነገሌ ከተማ እየተካሄደ ባለስ ሰልፍ  ከ10ሺ በላይ የሚገመቱ ነዋሪዎች መሳተፋቸውን የስልፉ አስተባበሪ አቶ ባጫ ጅማ ለኢዜአ  ገልጸዋል።

የህግ የበላይነት እንዲከበር የድርሻችንን እንወጣለን፣ በኦሮሞ ስም የሚንቀሳቀሱ የጥፋት ኃይሎች አጥብቀን እንቃወማለን ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ያገኙት የኖቤል ሽልማት የሀገራችንን ቀጣይ ሰላምና አንድነት የሚያሳይ ነው የሚሉ መፈክሮች በነዋሪዎች ከተስተጋቡት መካከል ይገኙበታል።

በተመሳሳይ የኢሉአባቦርእና ቡኖበደሌ ዞኖች ነዋሪዎች በየከተሞቻቸው እያደረጉት ባለው ስልፍ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኖቤል የሰላም ሽልማት አሸናፊ በመሆናቸው መደሰታቸውን ባሰሙት መፈክርና በሰጡት አስተያየት ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሀገሪቱ ሰላምና ብልፅግና እንዲረጋገጥ የሚያደርጉትን ጥረትእንደግፋለን ፣ የመደመር ፍልስፍና ኢትዮጵያንና የአፍሪካ ቀንድን ሰላም የሚያረጋግጥ ነው ሲሉም ባሰሙት መፈክሮች ገልጸዋል።

በሰልፉ ወጣቶች ሴቶች ፣ የመንግስት ሰራተኞችንና ሌሎችም የህብረተሰብ ክፍሎች እየተሳተፉ ነው።