በጮራ ወረዳ ጠብ መንጃና ጥይቶችን በህገ ወጥ መንገድ ሲያዘዋውር ነበር የተባለ ግለሰብ ተያዘ

378

መስከረም 30/2012በቡኖ በደሌ ዞን ጮራ ወረዳ ሁለት ክላሽንኮቭ ጠብ መንጃና 1ሺ948 ጥይቶች በህገ ወጥ መንገድ ሲያዘዋውር ነበር የተባለ ግለሰብ መያዙን ፖሊስ አስታወቀ::
እነዚህ የጦር መሳሪያዎች የተያዙት  ዛሬ ጠዋት የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3 – 61128 ኦሮ በሆነ ሚኒባስ ተሽከርካሪ ከጋምቤላ ወደ አዲስ አበባ ሲጓጓዝ  ነው::

በጮራ ወረዳ  ፖሊስ ጽህፈት ቤት የአካባቢ ፀጥታ ማረጋገጥ ስራ ሂደት መሪ ሳጅን ዋቅጋሪ ጋዲሳ ለኢዜአ እንዳሉት የጦር መሳሪያዎቹ በወረዳው   ቁምባቢ ተብሎ በሚታወቀው የፍተሻ ቦታ የጸጥታ አካላት ባደረጉት ፍተሻ ማግኘት ችለዋል።

የተገኘውም በጆንያ ተጠቅልለው በተሽከርካሪው ሞተር ውስጥ ተደብቀው ለማለፍ  ሲሞክሩ ነው።

የጦር መሳሪዎቹን በህገ ወጥ መንገድ  ሲያጓጉዝ ነበር የተባለው አሽከርካሪ ተይዞ  ምርመራ እየተደረገበት እንደሚገኝ ሳጅን ዋጋሪ አስረድተዋል።