በናይሮቢ የኢትዮጵያ ኤምባሲ የተሰማውን ደስታ ገለጸ

91

ኢዜአ፤ መስከረም 30/ 2012 በናይሮቢ የኢፌዲሪ ኤምባሲ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የ2019 የኖቤል የሠላም ሽልማት አሸናፊ በመሆናቸው የተሰማውን ደስታ ገልጿል።

ኤምባሲው በላከው መግለጫ ዶክተር አብይ አህመድ በመሪነት ላበረከቱት ጉልህ አስተዋጽኦ የተሰጠ ዓለም አቀፋዊ ዕውቅና መሆኑን እናምናለን ብሏል።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በሺዎች የሚቆጠሩ የፖለቲካ እስረኞች እንዲለቀቁ፤ ዲሞክራሲ በኢትዮጵያ እንዲያብብ፤ የፖለቲካ ምህዳሩን ማስፋት እንዲቻል እንዲሁም በኢትዮጵያ እርቀ ሰላም እንዲወርድ ያላሰለሰ እንቅስቃሴ ሲያደርጉ መቆየታቸውም ተጠቅሷል።

በተመሳሳይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምስራቅ አፍሪካ የትብብር ቀጠና እንዲሆን ላደረጉት ጉልህ አስተዋጽኦ እና ዲፕሎማሲያዊ ጥረት ለመደገፍ ቁርጠኝነታችንን ለመግለጽ ብሏል ኤምባሲው።

ሽልማቱ ለሰላም የተሰጠ በመሆኑ መላው ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች ከሰላም ጎን እንዲቆሙ የሚጋብዝ ታላቅ እድል እንደሆነ ያምናል ያለው ኤምባሲው፤ በራሱ እና ኬንያ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ስም ደስታና ኩራቱን ይገልጻል ብሏል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም