ኢንጂነር ታከለ ኡማ በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ መሸለም የደስታ መግለጫ መልእክት አስተላለፉ

116
መስከረም 30/2012 ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የ2019 ዓ.ም የኖቤል አሸናፊነታቸውን ተከትሎ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ የደስታ መግለጫ መልእክት አስተላልፈዋል። ምክትል ከንቲባው ባስተላለፉት መልእክት የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ የኖቤል ሽልማት አሸናፊ መሆን የመላ ኢትዮጵያዊያን ሽልማት መሆኑን ገልፀዋል። ''ሽልማቱ ኢትዮጵያ የተለያዩ ፈተናዎችን አልፋ እርቅና ሰላም ዋጋ ያለው መሆኑን የተረዳንበት አጋጣሚ ነው'' ሲሉም ተናግረዋል። ''ሽልማቱ ትልቅ ትርጉም ያለውና የሁላችንም እውቅና ነው'' ያሉት ምክትል ከንቲባው ለዚህም "እንኳን ደስ ያለን፣ እንኳን ደስ ያላቸሁ" በማለት የደስታ መግለጫ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።    
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም