የቱኒዚያ ፍርድ ቤት እጩ ፕሬዚዳንታዊ ተወዳዳሪው ናቢል ካሮይ ከእስር እንዲፈታ ውሳኔ አስተላለፈ

88
መስከረም 29/2012 የቱኒዚያ ፍርድ ቤት ዕጩ ፕሬዚዳንታዊ ተወዳዳሪ ናቢል ካሮይ እ.አ.አ ጥቅምት 13/2019 ከሚካሄደው ሃገራዊ  ምርጫ አስቀድሞ እንዲፈታ ውሳኔ  መተላለፉ ተነገረ፡፡ የ56 ዓመቱ ናቢል ካሮይ ነሃሴ ወር ላይ ሲካሄድ በነበረው የመጀመሪያ ዙር የምርጫ ዘመቻ ከመሰጠቱ በፊት ገንዘብ በማባከንና ግብር በማጭበርበር በሚል ክስ በቁጥጥር ስር መዋሉንም መረጃው አስታውሷል፡፡ ዕጩ ፕሬዚደንቱ እ.አ.አ ከ2017 ጀምሮ በምርመራ ላይ እንደሚገኝ ዘገባው ያስታወቀ ሲሆን በዚሁ ዓመት በወርሃ ነሃሴ  ችሎት ቀርበው እንደነበርም ተነግሯል፡፡ ችሎት ላይ የተቀመጠው ፍርድ ቤቱ ናቢል ካሮይ በአስቸኳይ ከእስር እንዲለቀቅ መወሰኑን የእጩ ፕሬዚደንቱ ጠበቃ ካማል ቢን ሞሳድ አስታውቀዋል፡፡ የናቢል ካሮይ  ቃል አቀባይ ሃተም ሚሊኪ እንደገለፁት ከሆነ ደግሞ የሰውየው ከእስር መለቀቅ ከባድ ሁኔታ ላይ የነበረችውን ቱኒዚያ በማዳን አደጋ ተጋርጦበት የነበረውን የሃገሪቱን ዲሞክራሲ ለመጠበቅ ያስችላል ሲሉም አክለዋል፡፡ የቱኒዚያው ፕሬዝዳንት ምርጫ ሃገሪቱን እ.አ.አ በ2011 ከተካሄደው የአረብ አብዮት በኋላ ሃገሪቱን ለረጅም ዓመታት ሲያስተዳድሯት የነበሩትን መሪ ዚኔ ኢል-አቢዲኔ ቤን አሊን ከስልጣን ከተወገደ በኋላ  ለሁለተኛው ጊዜ መሆኑንም መረጃው አስፍሯል፡፡ ፕሬዚዳንታዊ  ምርጫው የሚካሄደውም ለመጀመሪያ ጊዜ በዲሞክራሲያዊ መንገድ ተመርጠው ሃገሪቱን ሲያስተዳድሩ የነበሩት መሪ ቤጂ ሲያድ ኢሴበሲ ሃምሌ ወር ላይ ህይወታቸው ማለፍን ተከትሎ እንደሆነም ሲ ጂቲ ኤን የአፍሪካ ገፅ አስታውቋል፡፡
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም