የዩጋንዳው ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ አዲስ አበባ ገቡ

776

አዲስ አበባ ኢዜአ መስከረም 29/2012 የዩጋንዳው ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ የአንድነት ፓርክ የምረቃ ስነስርዓት ለመታደም አዲስ አበባ ገቡ

ፕሬዚዳንት ሙሴቬኒ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም ደማቅ አቀባባል ተደርጎላቸዋል።

የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሙሓመድ አብዱላሂ መሐመድ፣ የደቡብ ሱዳኑ ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር እንዲሁም የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክ እስካሁን የገቡ ሲሆን የኬንያው ፕሬዝዳንት ኡህሩ ኬንያታም ይገባሉ ተብሎ በመጠበቅ ላይ ናቸው።

እንግዶቹ አዲስ አበባ የገቡት በታላቁ ቤተ መንግስት የተገነባው የአንድነት ፓርክ ምረቃ ስነ ስርዓት ላይ ለመሳተፍ ነው።