የዚምባብዌ የኤሌክትሪክ ዋጋ በ320 በመቶ ጨምሯል ተባለ

59
ኢዜአ መስከረም 28/2012 የአገሪቱ ሃይል ተቆጣጣሪ መስሪያ ቤት እንዳስታወቀው በዚምባቡዌ አማካይ የኤሌክትሪክ ዋጋ ታሪፍ በ320 በመቶ ጨምሯል ፡፡ የዚምባቡዌ መንግሥት የኤሌክትሪክ ዋጋን ማስተካከያ ያደረገው በየዕለቱ የሚጋጥመውን የኃይል መቆራረጥ ለማስቀረት እና የሃይል አቅርቦት ለማሻሻል አልሞ ነው ተብሏል፡፡
የኤሌክትሪክ አቅራቢው ኩባንያ ኃይል ለማመንጨት ለጄነሬተሮች የሚያስፈልገው ነዳጅ መግዣ ተጨማሪ ገንዘብ እንደሚያስፈልገውም ተገልጿል፡፡ ዚምባብዌ ከ 2017ቱ የፕሬዚዳንት ሮበርት ሙጋቤ መፈንቅለ መንግስት ወዲህ ከፍተኛ የኢኮኖሚያዊ ቀውስ እንደገጠማትም ይነገራል፡፡ የአሁኑ በኤሌክትሪክ ዋጋ ጭማሪ በሶስት ወር ውስጥ ለሁለተኛ ግዜ የተደረገ ሲሆን ቀድሞም በነዳጅ እና በመሰረታዊ ፍጆታዎች የዋጋ ንረት ምክንያት በከባድ ጫና ውስጥ የቆዩት ዚምባብዌያንን አስቆጥቷቸዋል ፡፡ በዚምባቡዌ በየቀኑ ለ18 ሠዓታት የሃይል መቆራረጥ የሚያጋጥም ሲሆን ይህም በማዕድን ፣ ፋብሪካዎች እና በነዋሪዎች ላይ ትልቅ ጫና ፈጥሯል፡፡ በአገሪቱ የተከሰተው የኃይል እጥረት ከአስከፊ ድርቅ ጋር ተዳምሮ የዚምባብዌ ኢኮኖሚ ክፉኛ እንደጎዳውም ተገልጿል፡፡ ቢቢሲ
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም