ከ 50 በላይ ስደተኞችን የያዘች ጀልባ በሊቢያ ባህር ዳርቻ ተገለበጠች-የተባበሩት መንግስታት

109
ኢዜአ መስከረም 19/2012 ከ50 በላይ ስደተኞችን አሳፍራ የነበረች ጀልባ በሊቢያ የባህር ዳርቻ መገልበጧን የተባበሩት መንግስታት አስታወቀ ፤ጀልባዋ ጉዟቸውን ወደ አውሮፓ ያደረጉ ስደተኞችን አሳፍራ ነበር ፡፡ አደጋው የደረሰበት ትክክለኛ ቦታ በግልፅ አለመታወቁን የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ኤጀንሲ በቲውተር ገልጿል፣ የሊቢያ የባህር ጠባቂ ቃል አቀባይ እንዳሉት ቃኚ ጀልባ ወደ ስፍራው መላኩን ተናረው ተጨማሪ መረጃ ከመስጠት ተቆጥበዋል፡፡
አፍሪካውያን ስደተኞች ድህነትንና ጦርነትን በመሸሽ ወደ ጣልያን ለሚያደርጉት ጉዞ ሊቢያ ዋነኛ መዳረሻ ስትሆን አብዛኞቹም በሊቢያ ባህር ጠባቂዎቸ ተይዘው ይመለሳሉ ይህም በአውሮፓ ህብረት ድጋፍ የሚደረግ ነው፡፡ በሺዎች የሚቆጠሩ ስደተኞችም በሊቢያ መንግስት በሚተዳደሩ ማረሚያ ቤቶች የሚገኙ ሲሆን የሰብአዊ መብት ተሟጋቾችና የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች አያያዝን ኢሰብአዊ ነው ሲሉ ይደመጣሉ፡፡ ሲጂቲኤን አፍሪካ
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም