በበጎ አሳቢዎች የተጀመረው ማህበራዊ በጎ ፈቃደኝነት እንዲስፋፋ ፍትሃዊና ፈጣን ምላሽ ሰጪ አካል ያስፈልጋል - አስተያየት ሰጪዎች

106
አዲስ አበባ መስከረም 9/2012 የማህበረሰቡን ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ከፌዴራል እስከ ታችኛው መዋቅር ያሉ ተቋማት የትኩረት መስካቸውንና ድርሻቸውን ለይተው መሰማራታቸው ማህበራዊ ችግሮችን ለመፈታት ሚናው ከፍተኛ መሆኑን አስተያየት ሰጪዎቹ ገልጸዋል። ማህበራዊ ተጠያቂነት ሲጠናከር ከችግሮች መልሶ ማገገም የሚችል ማህበረሰብ መፍጠር እንደሚቻልም ገልጸዋል። ይህም እንደ ድርቅና መፈናቀል ያሉ ሰው ሰራሽና የተፈጥሮ አደጋዎችን በመቋቋም ለችግር የማይበገርና በራሱ መልሶ የማገገም አቅምን ለህብረተሰቡ ይፈጥራል። ሁሉም በየድርሻው ሃላፊነቱን ከተወጣ የመንግስትና የህዝብ ግንኙነቱን የሰመረ በማድረግ አገራዊ ዕድገትና የልማት ዕቅዱ ግቡን እንዲመታ ያስችላል። የባህርዳርከተማየማህበራዊተጠያቂነትኮሚቴጸሐፊአቶአበበብርሌለኢዜአእንደገለጹት፤የማህበራዊፍትሃዊተጠቃሚነትችግርመንስኤውምመፍትሔውምከአንድወገንየማይመጣነው። ከጤና፣ ከውሃ፣ ከመንገድ፣ ከመብራትና ከትምህርት ጋር ተያይዘው የሚነሱ ማህበራዊ ጥያቄዎችና ቅሬታዎች ለማስቀረት ፍትሃዊ ክፍፍሉንና ተደራሽነቱን የሚከታተል ደራሽ ሃይል መቋቋም እንዳለበት ገልጸዋል። እንደ አቶ አበበ፤ የደራሽ ሃይሉ መቋቋም በአገሪቱ እየተነቃቃ የመጣውና በበጎ አሳቢዎች ቅስቀሳ የተጀመረው ማህበራዊ በጎ ፈቃደኝነት እንዲስፋፋና ፍትሃዊ የሆነ ፈጣን ምላሽ ሰጪ አካል እንዲኖር ያስችላል። ይህም ለውጥ የማያስገኘውን የተናጠል ሩጫና ነጠላ እገዛና ድጋፍ ያስቀራል። ደረጃውን ጠብቆ የተደራጀ አገራዊ መዋቅር ካለ ማህበራዊ ቀውሶች ሲከሰቱ ወዲያው የት ምን ችግር እንደተፈጠረ? ለየትኞቹስ ቅድሚያ እንደሚሰጥ? በመለየት ፈጣን ምላሽ ለመስጠት ያስችላል። በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የማህበራዊ ልማት ኮሚሽን የነቀምት ቅርንጫፍ የማህበራዊ ፕሮጀክት አስተባባሪ አቶ ሰኚ ነጋሽ በበኩላቸው፤ "ማህበራዊ ተጠያቂነት ያላቸው ተቋማት ከተዋቀሩ በተለይ በአገራችን ከድርቅና ከስራ ዕድል አለመመቻቸት ጋር ተያይዘው ለሚፈጠሩ ችግሮች መፍትሔ እንዲሰጡ ያስችላል" ብለዋል። ''ተቋማቱ ችግር ከመከሰቱ በፊት ሁኔታውን ቀድመው በማሳሰብ እንደ ማንቂያ ደወል ያገለግላሉ'' ብለዋል። በአገራችንበማህበራዊተጠያቂነትናችግርአፈታትዙሪያበገጠሩየአገሪቱክፍልክፍተትእንዳለያነሱትአቶሰኚ፤ ''ማህበረሰቡምንመጠየቅናበማንምንመሰራትእንዳለበትግንዛቤስለሌለውየሚከሰትነው''ብለዋል። ይህንንም ለመፍታት እስከ ወረዳ ብቻ የነበረውን የተጠያቂነት አደረጃጀት ከወረዳ በላይ ሃላፊነት በሚጠይቁ ማህበራዊ ችግሮች ለመፍታት እስከ ፌዴራል የሚዘልቅ መዋቅር እንዲፈጠር የግንዛቤ የማስጨበጥ ስራ መጀመሩን ጠቁመዋል። ከፌዴራል ወደ ቀበሌ ሲወርድ የነበረው "ችግርህን እኔ አውቅልሃለሁ" ከሚል የማህበራዊ ችግር አፈታት ልማድ በመላቀቅ ከቀበሌ ወደ ፌዴራልም የሚዘረጋና ችግሩ መፈታቱን የሚያረጋግጥና ተጠያቂ የሚያደርግ አሰራር መኖር እንዳለበት አስተያየት ሰጭዎቹ ይስማሙበታል። በዚህም ከማህበራዊ በጀት አጠቃቀም ጋር ተያይዞ ለሚፈጠሩ ክፍተቶችና የፍትሓዊነት ጥያቄ የመንግስትና የግሉ ዘርፍ በጋራ ለችግሮቹ መፍትሔ እንዲያፈላልጉ ያስችላል። እነዚህን ችግሮች በጋራ መፍታት ከተቻለ መንግስት ትኩረቱን በታላላቅ ስራዎቹ ላይ በማዋል ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ ያስችለዋል ነው የተባለው።    
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም