በጎርጎሮሳውያኑ በ2018 ከ29 ሚሊዮን በላይ ህጻናት በግጭት ውስጥ ተወልደዋ

78

አዲስ አበባ መስከረም 9/2012 እ.አ.አ በ2018 አመት ከ29 ሚሊየን በላይ ህጻናት በግጭት በተጎዱ አካባቢዎች መወለዳቸውን የተባበሩት መንግስታት የህጻናት ፈንድ (ዩኒሴፍ) ገለጸ።

በግጭት በተጎዱ አካባቢዎች የሚገኙ ወላጆች ልጆቻቸውን ማሳደግ እንዲችሉም አለምቀፉ ማህበረሰብ ድጋፉን እንዲጨምር ዩኒሲፍ ለኢዜአ በላከው መግለጫ ጥሪ አቅርቧል።

በአለም ላይ ከአምስት ህጻናት አንዱ በፈራረሰና ግጭት ባለበት አካባቢ የሚወለድ ሲሆን የእርስ በእርስ ግጭት የማይጠፋባቸው አፍጋኒስታን፣ ሶማሊ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ሶሪያና የመን ተጠቅሰዋል።

ማንኛውም ወላጅ ልጁን በወለደ በመጀመሪያዎቹ ደቂቃዎች የሚሰማው የተለየ የደስታ ስሜት ቢሆንም ግጭት ባለባቸው አካባቢዎች ለሚኖሩ ወላጆች ግን ሰቀቀን መሆኑን በመግለጽ የችግሩን አስከፊነት የዩኒሴፍ ዋና ዳሬክተር ሄነሪታ ፎሪ ገልጸዋል።

በነዚህ አካባቢዎች በሚሊዮን የሚቆጠሩ ቤተሰቦች የምግብ፣ የንጹህ መጠጥ ውሃ፣ የንጹህና ሌሎች መሰረታዊ አቅርቦቶች የወደሙበት፤ ተወልዶ ለማደግ ቀርቶ ለሰከንድ እንኳን መቆየት በማያስች ሁኔታ ህጻናት ይህን ምድር እየተቀላቀሉ ይገኛሉ።

በጦርነትአካባቢዎችየሚወለዱናየሚያድጉህጻናትበሚያዩትአሰቃቂናየሚጎዳድርጊትየዘላለምህይወታቸውላይየስነልቦናጫናይፈጥራል።

ዩኒሴፍበየመን፣አፍጋኒስታን፣ደቡብሱዳን፣ሶማሊያየሚገኙህጻናትፍርሃት፣ጥርጣሬ፣እንቅልፍማጣትናሌሎችችግሮችውስጥእንደሚገኙበቅኝቱማረጋገጡንበመረጃውአካቷል።

በመሆኑም ለህጻናትና ወላጆች ምቹ አካባቢ፣ የጤና ተቋም፣ የስነልቦና ድጋፍና ሌሎች የሰብዓዊ እርዳታ እንደሚያስፈልግ ተገልጿል።

ከ29 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ህጻናት ህይወትና የወደፊት ተስፋ አሁን ላይ አገሮችና አለም አቀፍ ድርጅቶች በሚሰሩት ተግባር ላይ የተመሰረተ በመሆኑ ትኩረት እንዲሰጠው ዩኒሴፍ ጥሪ አቅርቧል።