የናይጄሪያ ጦር የቦኮ-ሃራም ታጣቂዎችን ይመግባሉ ያሏቸውን የተራድኦ ድርጅቶች ቢሮ አገደ

87
መስከረም 9/2012 የናይጄሪያ ጦር በሰሜናዊ ምስራቅ የሀገሪቱ ክፍል የቦኮ-ሃራም ታጣቂዎችን ትረዳላቹህ በሚል ክስ አለም ዓቀፍ የተራዶ ድርጅቶችን እንቅስቃሴ መዝጋቱ ተዘገበ፡፡ ይህ እርምጃ የተወሰደው ምግብ ለተራቡ የተሰኘ ተራዶ ድርጅት ለእስላሚክ አመፀኞች የምግብና እፅ አቅርቦት ይሰጣል በሚል ሰበብ እንደሆነም መረጃው አስፍሯል፡፡ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶቹ በበኩላቸው ወታደሮች ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ በሰሜን ምስራቅ ቦርኖ ግዛት ማይዱጉሪ ከተማ ያለው  ቢሯቸው የመዝጋቱን ክስ አልተቀበሉትም፡፡ ይህ ውሳኔ  ምግብ ለተራበ የተሰኘ ተራዶ ድርጅት ቦርኖ ግዛት ውስጥ  በጣም ተጋላጭ ለሆኑ ሰዎች የሚሰጠውን ድጋፍ ከማደናቀፍ ባለፈ ማይዱጉሪ፣ ሞነጉኖና ዳማሳክ ከተሞች ውስጥ  ያሉ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ተረጂ ሰዎችንም ተፅዕኖ ውስጥ ይከታቸዋል ሲል ሮይተርስ መዘገቡን ቢቢሲ ጠቅሷል፡፡ በሰራዊቱ የቀረበው ክስ እጅግ በጣም ከባድ እና  የተራዶ ድርጅቶችን ተግባርም ሆነ  ሰራዊቱ በቀጠናው የሚያደርገውን የደህንነትና የፀረ-ሽብርተኝነት ስራ ያስተጓጉልበታል ተብሏል፡፡ ከዚህ ቀደምም ቢሆን ምግብ ለተራበ የተሰኘው አለም ዓቀፉ ተራዶኦ ድርጅት አሸባሪዎችን ይረዳሉ በሚል የተለያዩ ማስጠንቀቂያዎች ተሰጥቷቸው እንደነበር አጃንስ ፋራንስ ፕሬስ ዜና ኤጀንሲ መግለፁንም መረጃው አስፍሯል፡፡ ሰራዊቱ በመግለጫው ክሱን የሚያጠናክሩ ተዓማኒነት ያላቸው ማስረጃዎች ማግኘቱን  ዘገባው ጠቁሟል፡፡ የቦኮ-ሃራም ታጣቂ  በናይጀሪያ ሰሜናዊ የሀገሪቱ ክፍል ከ10 ዓመት በላይ የሽምቅ ውጊያ ሲያደርግ መቆየቱን ያስታወሰው ዘገባው ጎረቤት ቻድ፣ ኒጀርና ካሜሮንንም ጭምር የገፈቱ ተቋዳሽ አድረጓቸው ቆይቷል፡፡ በግጭቱ  ምክንያት በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ ንፁሃን ሲገደሉ ከሁለት ሚሊዮን በላይ የሚጠጉት ደግሞ ቤት ንብረታቸውን ለቀው ለመሰደድ ተገደዋል፡፡ ቡድኑ እ.አ.አ 2014 በቡርኖ ግዛት ቺቦክ ከተማ በአንድ ትምህርት ቤት ውስጥ 200 የሚሆኑ ልጃገረዶችን ጠልፎ ከወሰደ ብኋላ አለም ዓቀፍ ሚዲያዎችን ቀልብ እንደሳበም ዘገባው አስታውሷል፡፡  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም