በታች አርማጭሆ ወረዳ ከ3ሺህ 500 በላይ ህገ-ወጥ የብሬን ጥይት ተያዘ

128
መስከረም 07/2012 በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ታች አርማጭሆ ወረዳ 3 ሺህ 555 ህገ-ወጥ የብሬን ጥይት መያዙን የሳንጃ ጉምሩክ መቆጣጠሪያ ጣቢያ አስታወቀ። የመቆጣጠሪያ ጣቢያው አስተባባሪ ኮማንደር ሞላ ተሾመ ለኢዜአ እንዳስታወቁት ጥይቱ የተያዘው ከዳንሻ ወደ ጎንደር ሲጓዝ በነበረ የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3 አአ 84556 በሆነ ፒካፕ መኪና ላይ ትናንት ከቀኑ 11፡00 ሰዓት በተደረገ ፍተሻ ነው፡፡ አሽከርካሪው መቆጣጠሪያ ጣቢያውን ጥሶ ለማለፍ ሙከራ ቢያደርግም በፀጥታ ሃይሉ ጥረት በማስቆም በተካሄደ ፍተሻ  በመቀመጫ ወንበሩ ስር ደብቆት የተገኘውን ጥይት መያዝ እንደተቻለ አስታውቀዋል። አሽከርካሪው በቁጥጥር ስር ውሎ ጉዳዩ በህግ እየታየ መሆኑንም አስታውቀዋል። ህዝቡ የሚጠራጠረው እንቅስቃሴ ካለ ለሚመለከተው አካል ጥቆማ በመስጠት ለሰላምና መረጋጋት የድርሻውን እንዲወጣም አሳስበዋል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም