የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ከምዕራብ ኦሞና ቤንች ሸኮ ዞኖች ነዋሪዎች ጋር እየተወያዩ ነው

67
መስከረም ኢዜአ 5/2012 የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳው ከምዕራብ ኦሞና ቤንች ሸኮ ዞኖች ነዋሪዎች ጋር በሚዛን አማን ከተማ እየተወያዩ ነው ፡፡ በውይይቱ የደኢህዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻን ጨምሮ የክልልና የዞኖቹ አመራሮች ተገኝተዋል ፡፡ ነዋሪዎቹ በውይይቱ ወቅት በአካባቢያቸው ያሉ የመሰረተ ልማትና የፀጥታ ችግሮች እንዲፈቱላቸው ጠይቀዋል፡፡ ነዋሪዎቹ ላነሷቸው ሌሎችንም ጥያቄዎች  የክልሉ ምክትል ርዕሰ መሰተዳደር ምላሽ እንደሚሰጡ  ይጠበቃል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም