መንግስት ዜጎች ተከባብረው የሚኖሩባትና ታላቋን ኢትዮጵያን ለመፍጠር የሚያደርገውን ተግባር አጠናክሮ ይቀጥላል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ

82
አዲስ አበባ መስከረም 4/2012  መንግስት ዜጎች ተከባብረው የሚኖሩባት ታላቋን ኢትዮጵያን ለመፍጠር የሚያደርገውን ተግባር አጠናክሮ እንደሚቀጥል ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን የተናገሩት በከፋ ዞን ቦንጋ ከተማ ተገኝተው ለነዋሪዎች ባደረጉት ንግግር ነው። ቂም፣ ተንኮልና ባለፈ ታሪክ መነታረክ የሚያተርፉት ድህነትን ብቻ እንደሆነም አመልክተዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አክለውም፤ የከፋ ህዝብ ከሰው ጋር ብቻ ሳይሆን ከተፈጥሮ ጋር ተስማምቶ የኖረ አስተዋይ ህዝብ መሆኑን ገልጸዋል። ከጠቅላይ ሚኒስትሩ በተጨማሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን፣ የመከላከያ ሚኒስትር ለማ መገርሳ፣ የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ርስቱ ይርዳና ሌሎች የመንግስት የስራ ኃላፊዎችም በቦታው ተገኝተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሰዓት በኋላ ከቦንጋ ከተማና አካባቢው ማህበረሰብ ተወካዮች ጋር ይመክራሉ ተብሎም ይጠበቃል።    
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም