ዲላ ዩኒቨርሲቲ 2ሽህ 286 ተማሪዎች አስመረቀ

95
ዲላ ኢዜአ ነሐሴ 30 ቀን 2011፡- የዲላ ዩኒቨርስቲ በክረምት ወራት ያሰለጠናቸውን 2ሽህ 286 ተማሪዎች ዛሬ በመጀመሪያና በሁለተኛ ዲግሪ አስመረቀ። ዩኒቨርሲቲው ካስመረቃቸው ተማሪዎች ውስጥ 504 ሴቶች ይገኙበታል። የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶክተር ችሮታው አየለ በወቅቱ እንደገለጹት ከእለቱ ተመራቂዎች192 በሁለተኛ ድግሪ ትምህርታቸውን የተከታተሉ ናቸው። ተመራቂዎች በቋንቋ፣ ሂሳብ፣ ፊዚክስ፣ ባውሎጂና በሌሎች ዘርፎች የሰለጠኑ መሆናቸውን ተናግረዋል። ተመራቂዎች በትምህርት ቆይታቸው የቀሰሙትን እውቀት በመጠቀም ህብረተሰቡን በአግባቡ እንዲያገለግሉ ፕሬዝዳንቱ መልእክት አስተላልፈዋል ። የእለቱ ተመራቂዎች በበኩላቸው የትምህርት ደረጃቸውን ማሻሻል መቻላቸው ስራቸውን በጥራትና በብቃት እዲወጡ አቅም የሚፈጥረላቸው መሆኑን ተናግረዋል ። አንተነህ መላኩ በሂሳብ  ትምህርት ክፍል በከፍተኛ ማዕረግ የተመረቀው ሲሆን መንግስት ባመቻቸለት የትምህርት እድል የትምህርት ደረጃውን ማሻሻል በመቻሉ መደሰቱን ገልጿል። "በትምህርት ቆይታየ ያገኘሁት እውቀትና ክህሎት ብቃት ያለው ተማሪን ለማፍራት የሚያስችለኝን አቅም ፈጥሮልኛል " ብሏል ። "በማስተማር ስራዩ ላይ ሆኘ የትምህርት ደረጃየን ማሻሻል በመቻሌ ደስተኛ ሆኛለሁ" ያለችው ደግሞ ሌላዋ ተመራቂ  ምንትዋብ ክፍሌ ናት። በትምህርት ቆይተዋ ያገኘችውን እወቀት ስራዋን በጥራትና በብቃት እንድተፈፅም የሚያግዛት  መሆኑን ገልጻለች ። የዲላ ዩኒቨርስቲ  በመደበኛ መረሃ ግብር ከሚያሰለጥናቸው ተማሪዎች በተጓዳኝ በክረምትና በእረፍት ቀናት መረሃ ግብር ከ10 ሺህ በላይ ተማሪዎችን እያስተማረ እንደሚገኝ ተመልክቷል።  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም