ሁዋዌ አሜሪካን በሳይበር ጥቃት ከሰሰ

89
ኢዜአ ነሃሴ 29/2011 የቻይና የቴክኖሎጂ አምራች ኩባንያ ሁዋዌ የአሜሪካ መንግሥት የሳይበር ጥቃት በማድረስ በስራው ላይ ጫና እንደፈጠረበት በመግለፅ ድርጊቱን ኮንኗል። በአሜሪካ የንግድ ጥቁር መዝገብ የሰፈረው የቴክኖሎጂ ተቋም እንዳለው ሰራተኞቹም ስለድርጅታቸው መረጃ እንዲሰጡ በኤፍ ቢ አይ ባልደረቦች ጫና ውስጥ ወድቀዋል።
በአሜሪካ እና በቻይና መካከል የንግድ ዋነኛ ውዝግብ የሆነው ሁዋዌ በመረጃ መረብ የኔትወርክ ስርዓቱና በሰራተኞቹ ላይ ደረሰ ስላለው ጉዳት አሳማኝ ማስረጃ እንዳልጠቀሰም ተነግሯል። ሁዋዌ ስላወጣው የውንጀላ መግለጫ ከአሜሪካ በኩል እስካሁን የተሰጠ ምላሽ የለም ሲል ቢቢሲ በዘገባው ጠቅሷል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም