በደቡብ አፍሪካ በተቀሰቀሰው አመፅ መንግስታት ማስጠንቀቅያ እየሠጡ ነው

131
ኢዜአ ነሃሴ 28/2011በደቡብ አፍሪካ ባለቤትነታቸው የውጭ ዜጎች የሆኑ የንግድ ማዕከላት ኢላማ ያደረገ አመፅ መቀስቀሱን ተከትሎ በርካታ የአፍሪካ ሃገራት ለዜጎቻቸው ደህንነት በማሰብ ማስጠንቀቅያ እየሰጡ ይገኛሉ፡፡ በደቡብ አፍሪካ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ እንዳስታወቀው የንግድ ማእከል በሆነችው ጆሀንስበርግ ኢትዮጵያውያን ሱቆቻቸውን ከዝርፊያና ከቃጠሎ ለመታደግ እንዲዘጉ አሳስቧል፡፡
በሌላ በኩል የዚምባብዌ ትራንስፖርት ሚኒስቴር በደቡብ አፍሪካ ያለው ሁኔታ እስኪረጋጋ ድረስ የጭነት መኪኖች ወደዛ መጓዝ እንደሌለባቸው አስጠንቅቋል፡፡ እየወጡ ያሉ ዘገባዎችን መሰረት በማድረግም ሚኒስቴሩ የውጭ ሃገራት ከባድ መኪኖች ኢላማ መደረጋቸውንና በርካቶች መዘረፋቸውንም አስታውቋል፡፡ የናይጄርያ መንግስት በበኩሉ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጎኦፍሪ ኦንየማ የቲውተር ገፅ እንዳስቀመጠው ጥቃቱ በዋነኝነት በናይጄርያ የንግድ ስራ ላይ ያነጣጠረ መሆኑን ገልፆ “ይበቃቹሃል” የሚል መልእክት አስተላልፏል፡፡ ሰኞ እለት የደቡብ አፍሪካ የፖሊስ ሚኒስትር በሀኪ ሰሌ እንዳሉት አመፁ ከውጪ ሃገር ሰዎች ጥላቻ ይልቅ ወደ ወንጀል ያመዝናል ፤”ግብ የለሽ ድርጊት” ሲሉም አውግዘውታል፡፡ ምንጭ፡-ቢቢሲ
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም