የአሸንዳዬ ሻደይና ሶለል የልጃገረዶች በዓል በዩኔስኮ የማይደሳሱ ቅርሶች ዝርዝዝር ውስጥ እንዲካተት የተጀመረውን ጥረት ሁሉም ሊደግፈው እንደሚገባ የኢፌድሪ ፕሬዝዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ አስገነዘቡ

101
ነሀሴ19/2011 የአማራ ሴቶች ማህበር አዲስ አበባ ቅርጫፍ ያዘጋጀው የበዓሉ ማጠቃላይ ዛሬ በሚሊኒየም አዳራሽ ተካሂዷል። በበዓሉ ላይ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴን ጨምሮ፣የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ዑማ፣የአማራ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ተመስገን ጥሩነህና የፌደራልና የክልል ባለስልጣናት ተገኝተዋል። በተለያዩ ባህላዊ አልባሳት የታጀበ ውዝዋዜና የልጃገረዶች ጫዋታ እንዲሁም ባህላዊ ምግብና መጠጥ ትዕይንቶችም የመርሃ ግብሩ አካል ነበሩ። ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ኢትዮጵያ የማይዳሰሱ ቅርሶችን በዩኔስኮ በማስመዝገብ ረገድ ከአፍሪካ ከቀዳሚዎቹ ተርታ ትሰለፋለች። ''ቅርሶቻችን የኛ ብቻ አይደሉም'' ያሉት ፕሬዝዳንቷ ይሄንን በዓል የዓለም ቅርስ ሆኖ እንዲመዘገብ ሁላችንም የድርሻንን መወጣት ይኖርብናል ብለዋል። የቀደሙት እናትና አባቶች የቆይቱን ባህልና ትውፊት በመንከባከብ ለቀጣዩ ትውልድ ማስተላለፍ ከኛ የሚጠበቅ ተግባር ነው ሲሉም ተደምጠዋል።          
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም