መቀሌ በዩኒቨርሲቲዎች ሰላማዊ የትምህርት አሰጣጥ ላይ ያተኮረ ጉባዔ እያስተናገደች ነው

128

መቀሌ ነሐሴ 19 ቀን 2011በቀጣይ ዓመት በዩኒቨርሲቲዎች የትምህርት አሰጣጥ ሰላማዊ በሚሆንበት መንገድ ላይ የሚመክር ጉባዔ በመቀሌ እየተካሄደ ነው።
ጉባዔውን የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ኅብረት “የ2012 የትምህርት ዘመን ሰላማዊና ብሩህ እናደርጋለን!” በሚል መርህ ያዘጋጀው ነው።

የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ክንደያ ገብረ ሕይወት በዚሁ ወቅት እንደተናገሩት ዩኒቨርሲቲዎች ሰላማቸው ተጠብቆ የትምህርት ጥራትን ማረጋገጥ ይጠበቅባቸዋል።

በቀጣይ ዓመት በዩኒቨርሲቲዎች ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት በመፍጠር ተማሪዎች በዕውቀት፣ በክህሎትና በአመለካከት ታንጸው እንዲወጡ ኅብረቱ ድርሻውን መወጣት አለበት ብለዋል።

ዩኒቨርሲቲዎች ትምህርት የሚቀሰምባቸው እንጂ፤ተማሪዎች በብሔራቸው ምክንያት የሚጠቁበት ሊሆን አይገባም ያሉት ፕሬዚዳንቱ፣ይልቁንም የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ መሰራት እንዲሰራ አሳስበዋል።

የኅብረቱ ፕሬዚዳንት ይድነቃቸው አየለ በበኩሉ ጉባዔው በ2011 የነበሩ ችግሮችን በመገምገም 2012 ሰላማዊ የትምህርት ዘመን እንዲሆን ለማድረግ መዘጋጀቱን ገልጿል።

እንዲሁም መልካም እሴቶችን መንገድ ላይ ውይይት ይደረጋል ብለዋል።

ለሶስት ቀናት በሚቆየው ጉባዔ ከ46 ዩኒቨርሲቲዎች የተውጣጡ 180 ተማሪዎች እየተሳተፉ ነው።