የብሪታኒያ የዓለም ዓቀፍ ልማት ሚኒስትር ከኦሮሚያ ምክትል ፕሬዚዳንት ጋር በመሆን የኢስተርን ኢንዱስትሪ ዞንን ጎበኙ

68
ነሀሴ16/2011 የብሪታኒያ የዓለም ዓቀፍ ልማት ሚኒስትር አሎክ ሻርማ ከኦሮሚያ ምክትል ፕሬዚዳንት ሽመልስ አብዲሳ ጋር በመሆን የኢስተርን ኢንዱስትሪ ዞን የሚገኘውን ዩኒሊቨር ፋብሪካን ጎብኝተዋል። በጉብኝቱ ወቅት የኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ እንደገለጹት፤ የውጭ ኢንቨስተሮችን ለመቀበል በቂ ዝግጅት አለ። ክልሉ በኢንቨስትመንት ለመሰማራት የሚመጡ የውጭ ባለሃብቶችን  ውጤታማ  ሆነው የአገሪቱን ኢኮኖሚ እንዲደግፉ  ምቹ ሁኔታ መፈጠሩን አስታውቀዋል። የብሪታኒያ የዓለም ዓቀፍ ልማት ሚኒስትር አሎክ ሻርማ በበኩላቸው ሰፊ የስራ ዕድል በሚፈጥሩ የኢንቨስትመንት መስኮች የብሪታኒያ ባለሃብቶች እንዲሰማሩ ድጋፍ እንደሚያደርግ ጠቁመዋል። በተለይም ለሴቶች የስራ ዕድል በሚፈጥሩ መስኮች ላይ ትኩረት የሚደረግ መሆኑን ተናግረዋል። ሃላፊዎቹ ጉብኝቱን ካጠናቀቁ በኋላ የችግኝ ተከላ አካሂደዋል።    
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም