በካቡል በሰርግ ስነስርኣት ላይ በተፈጸመ የቦምብ ጥቃት 63 ሰዎች ተገደሉ

68

ኢዜአ ነሃሴ 12/2011 በአፍጋኒስታን ዋና ከተማ ካቡል በተፈጸመ የቦምብ ጥቃት የ63 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ 180 ቆስለዋል፡፡

የአይን እማኖች ለቢቢሲ እንደተናገሩት ቦምብ የታጠቀ አጥፍቶ ጠፊ በሰርግ ስነስርአቱ ላይ ፍንዳታ አስከትሏል፡፡

የተፈጸመው ጥቃት በከተማዋ ምእራባዊ ክፍል የሚገኝና የሺአ ሙስሊሞች በሚገኙበት አካባቢ መሆኑም ታውቋል፡፡

በጥቃቱ ታሊባን እጁ እንደሌለበት ያስታወቀ ሲሆን እስካሁን ኃላፊነቱን የወሰደ አካል የለም፡፡

ሺአ ሃዛራ በተሰኙት የማህበረሰብ ክፍሎች የሱኒ ሙስሊም ታጣቂዎችን ጨምሮ ታሊባንና የአይ ኤስ ታጣቂ ቡድን በአፍጋኒስታንና በፓኪስታን ተደጋጋሚ ጥቃት እያደረሱባቸው ይገኛል ብሏል ዘገባው፡፡

የአፍጋኒስታን የጤና ባለሙያዎች ቁስለኞችን በመርዳት ላይ እየተረባረቡ መሆኑን ነው የቢቢሲ ዘገባ ያመለከተው፡፡