ፍርድ ቤቱ በመፈንቅለ መንግስት ወንጀል ሙከራ የተጠረጠሩ ተከሳሾች የምስክሮችን ቃል በመቀበል ውሎውን አጠናቀቀ

46
ባህርዳር  ነሓሴ 9/2011 የባህርዳርና አካባቢዉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዛሬ ባስቻለቸው ችሎት በአማራ ክልል ሰኔ 15/2011 ዓ.ም ተፈጽሟል በተባለው የመፈንቅለ መንግስት ወንጀል በተጠረጠሩ የቅድመ ክስ ምርመራ ላይ የሶስት ምስክሮችን ቃል በመቀበል ውሎን አጠናቀቀ። ፍርድ ቤቱ የምስክርነት ቃል የተቀበለው በእነ የማነ ታደሰ መዝገብ ስር በተከሰሱ 48 ተጠርጣሪዎች ላይ ነው። በቅድመ ክስ ምርመራው የምስክርነት ቃል የመቀበል ሂደቱ የሌሎች ምስክሮችን ቃል ለመቀበል ነገም እንደሚቀጥል ፍርድ ቤቱ ቀጠሮ በመያዝ የዛሬ ውሎውን አጠናቋል። በአማራ ክልል ሰኔ 15/2011 ዓ.ም ተፈጽሟል በተባለው የመፈንቅለ መንግስት በመጠርጠር ተይዘው ከነበሩት 218 ሰዎች ውስጥ ብዙዎቹ ጉዳያቸው እየተጣራ መለቀቃቸውን በማስታወስ ሪፖርተራችን ከስፍራው ዘግቧል።    
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም