በዲሞክራቲክ ኮንጎ ከኢቦላ የተረፉ ሰዎች ቤተሰቦቻቸውን ተቀላቀሉ

129

ኢዜአ ነሃሴ 8/2011 ሁለት የሙከራ መድኃኒቶችን በመጠቀም ከኢቦላ በሽታ የተፈወሱ ሁለት ሰዎች በምስራቃዊ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ከሚገኘው ህክምና ማዕከል ወጥተው ከቤተሰቦቻቸው ጋር እንደተቀላቀሉ ቢቢሲ ዘገበ ፡፡

ከበሽታው የተፈወሱት ሰዎች በጉማ አራት ከሚሆኑ ምርመራ ከተደረገላቸው ሰዎች መካከል እንደነበሩ ሲገለፅ የኢቦላ በሽታ እስካሁን ቢያንስ 1ሺ 800 ሰዎችን የገደለና ከተማዋም በወረርሽኝ የተጎዳች ትልቋ ከተማ እንደሆነች በመረጃው ተጠቅሷል።

በቡድኑ ውስጥ የነበሩ ሁለት ሌሎች ሰዎች ከበሽታው ለመትረፍ አለመቻላቸውን መረጃው አክሏል።

ይሁን እንጂ ሳይንትስቶች ለሁለት መድኃኒቶች ክሊኒካዊ ሙከራዎች ካደረጉ በኋላ ኢቦላ በቅርቡ ሊከላከሉት እና ሊታከም የሚችል በሽታ እንደሚሆን ተስፋ እንዳደረጉ ተገልፅዋል፡፡

ዶ/ር ሳቢዬ ሙላንጉ ህክምና ከተደረገላቸው 681 ታካሚዎች መካከል 60በመቶ የሚሆኑት በሕይወት ሊተርፉ እንደቻሉ ገልፀዋል፡፡

ተመራማሪዎቹ ታማሚዎች አስቸኳይ ምርመራ እና ህክምና ከተደረገላቸው ከ 90 በመቶ በላይ የሚሆኑት አርኢጂኤን-ኢቢ3 እና ኤም ኤብ114 ከተሰጣቸው በሕይወት ሊተርፉ ይችላሉ ሲሉ መናገራቸውን በመረጃው ተጠቅሷል።