አምባሳደር ዶክተር ሽፈራው ተክለማሪያም የሹመት ደብዳቤያቸውን ለናሚቢያ ፕሬዚዳንት አቀረቡ

94
አዲስ አበባ ሰኔ 6/2010 አምባሳደር ዶክተር ሽፈራው ተክለማሪያም የሹመት ደብዳቤያቸውን ለናሚቢያ ፕሬዚዳንት ዶክተር ሐጌ ጎይንጎብ አቀረቡ። አምባሳደር ዶክተር ሽፈራው ኢትዮጵያና ናሚቢያ ያላቸውን ጠንካራና የቆየ ታሪካዊ ግንኙነት ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሳደግ እንደሚሰሩ የሹመት ደብዳቤያቸውን ባቀረቡት ወቅት መግለጻቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት አስታውቋል። በሁለቱ አገሮች መካከል በቱሪዝም፣ በዓሳ ሀብት ልማት፣ ትራንስፖርትና ግብርና ዘርፎች ግንኙነቱን ማጠናከር አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል። ፕሬዚዳንት ዶክተር ሐጌ ጎይንጎብ በበኩላቸው ኢትዮጵያ ለናሚቢያ ነጻነት ትግል ያደረገችውን ድጋፍ በማስታወስ በአገሮቹ መካከል ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል። አምባሳደር ዶክተር ሽፈራው ለሁለቱ አገሮች የጋራ ተጠቃሚነት ለመስራት መንግስታቸው ማንኛውንም ትብብርና ድጋፍ እንደሚያደርግ ቃል ገብተዋል። አምባሳደሩ በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ ከተማ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በመሆን ኢትዮጵያ ከናምቢያ ጋር የምታከናውናቸውን የዲፕሎማሲ ስራዎች እንደሚሸፍኑ የቃል አቀባይ ጽህፈት ቤቱ መረጃ ያመለክታል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም