የኢቦላ ቫይረስ 90 ከመቶ ታማሚዎችን የሚያድኑ መድሃኒቶች በምርምር ተገኝተዋል ተባለ

96
ኢዜአ ነሃሴ 7/2011 በዲሞክራቲክ ሪፓፕሊክ ኮንጎ በኢቦላ በሽታ ላይ ከተሞከሩ አራት የመዳህኒት አይነቶች መካከል በሁለቱ ላይ መልካም ውጤት ከታየ በኋላ የቫይረሱን ስርጭት መከላከል እና ማከም የሚቻል መሆኑን ሳይንቲስቶች ገለፁ ፡፡ ቫይረሱ በስፋት በሚስተዋልባቸው የዲሞክራቲክ ሪፓፕሊክ ኮንጎ አካባቢዎች አራት የመዳህኒት አይነቶች የተሞከሩ ሲሆን ከነዚህ መካከል ሁለቱ ጥሩ ውጤት ታይቶባቸዋል።
እንደ ሀገሪቱ የጤና ሚኒስትር ገለፃ አዲስ የተገኙ መድሃኒቶች የበሽታው ስርጭት በስፋት በተከሰተባቸው ስፍራዎች ጥቅም ላይ ለማዋል እየተሰራ ነው። ምርምርሩን ያስተባበረው የአሜሪካው የአለርጂ እና ተላላፊ በሽታዎች ኢንስቲቲዩሽን የተገኘው ውጤት ኢቦላን ለመዋጋት በጣም ጥሩ ዜና ነው ሲል ገልጿል ፡፡ በዲሞክራቲክ ሪፓፕሊክ ኮንጎ በሽታው ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ እስካሁን ድረስ ከ1 ሽህ 800 በላይ ሰዎች ህይወታቸው አልፏል። ምንጭ፡-ቢቢሲ
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም