አረፋ በጅግጅጋ ተከበረ

63
ጅግጅጋ ነሐሴ 5 ቀን 2011 የኢድ አል አድሐ (አረፋ) 1440ኛውን በዓል ዛሬ በጅግጅጋ ከተማ ተከብሯል:: በዓሉ በጅግጅጋ ስታዲዬም የተከበረው በዓል ሃይማኖታዊ  ሥርዓቱን ጠብቆ ነው። በጅግጅጋ ከተማና አከባቢዋ የሚኖሩ የእስልምና እምነት ተከታዮች በዓሉን በሶላት ሥነ-ሥርዓት ለማክበር ወደ ተዘጋጀው መግባት የጀመሩት ከጠዋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ ነበር። በዓሉ የሃይማኖት አባቶች፣ የእምነቱ ተከታዮችና የመንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት በተገኙበት ተከብሯል። የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ ሙሐመድ በአገር የተጀመረው ለውጥ የክልሉ ሕዝብ የእምነት ነፃነቱን ጠብቆ ሃይማኖታዊ እሴቶቹን ለማሳደግ ምቹ ሁኔታዎች እንደፈጠረለት ገልጸዋል። "የአዲሱ የክልሉ መንግሥት በተጠናቀቀው ዓመት ባስመዘገበው ስኬት ኅብረተሰቡ በመንግስት በኩል የሚደርስበት ስጋት ተላቋልል።አሁን መንግሥታዊ ሽብርተኝነት የለም ማንም ሰው በነፃነት መኖር ጀምረዋል" ብለዋል ። ​ ሕዝቡ ከመንግሥት ጋር በሰላም በልማት ጉዳዮች ላይ እንዲሰራም ጠይቀዋል ። የክልሉ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሼህ አህመድ አቢ በበኩላቸው በበዓሉ የተቸገሩ ወገኖችን  መርዳት በተለይም እርድ ለመፈጸም አቅም ያጡ ወገኖችን በመደገፍ እንዲከበር አሳስበዋል።      
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም