ካናዳ ሜክሲኮና አሜሪካ የ2026 የዓለም ዋንጫን በጥምረት እንዲያዘጋጁ ተመረጡ

611

አዲስ አበባ ሰኔ 6/2010 የ2026 የዓለም ዋንጫ የሰሜን አሜሪካ አገራት እንዲያዘጋጁ ተመረጡ።

ዛሬ በሩሲያ በተካሄደው 68ኛው የፊፋ ጉባዔ ላይ እንደተገለጸው የ2026 የዓለም ዋንጫ ካናዳ ሜክሲኮና አሜሪካ በጥምረት እንዲያዘጋጁ ወስኗል፡፡

ከ203 የፊፋ አባል አገራት መካከል 134 በዋንጫው በጥምረት እንዲያዘጋጁ ድምጽ የሰጡ ሲሆን የአፍሪካዋ አገር ሞሮኮ 65 ድምጽ ማግኘቷ ተገልጿል።

የሰሜን አሜሪካ አገራት የዓለም ዋንጫን ሲያዘጋጁ በ1994 እኤአ አሜሪካ ካዘጋጀች ወዲህ የመጀመሪያ ነው።

ለመጀመሪያ ጊዜ የተሳታፊ አገራት ብዛት ከ32 በ2026 የዓለም ዋንጫ ላይ ወደ 48 አገራት እንዲያድግ የቀረበው ሐሳብ ገና ውይይት እየተደረገበት ይገኛል።