የተከዜ ድልድይ በደለል በመሞላቱ በአካባቢው የተቋረጠው የትራንስፖርት አገልግሎት ለማስጀመር ጥረት እየተደረገ ነው

65
ነሀሴ 3/201 በተከዜ ወንዝ ላይ ተገነባው ድልድይ ደለል ሞልቶት በመሰናከሉ የተቋረጠው ከሰቆጣ- ጽጽቃ- መሸሃ የሚወስደው የትራንስፖርት አገልግሎት ለማስጀመር ጥረት እየተደረገ መሆኑን የዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር መንገድ እና ትራንስፖርት መምሪያ አስታውቀ፡፡ የመምሪያ ኃላፊ አቶ ሰለሞን እሸቱ ለኢዜአ እንደገለፁት ትራንስፖርቱ የተቋረጠው ሃምሌ 29/2011 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ በየለው ከባድ ዝናብ ተከትሎ የተከዜ ድልድይ በደለል እንዲሞላ በማድረጉ ነው። በደረሰው የደለል መሞላት ምክንያትም ከሰቆጣ ተነስቶ በፅፅቃ ከተማ ወደ ሰሃላ ሰየምት ወረዳ ይደረግ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ሙሉ በሙሉ መቋረጡን አስታውቀዋል፡፡ ቸግሩን በመፍታት የተቋረጠውን የትራንስፖርት አገልግሎት ለማስጀመር ጥረት እየተደረገ መሆኑን ያመለከቱት ኃላፊው ህብረተሰቡም ያጋጣመውን ችግር ተረድቶ በትዕግስት እንዲጠባበቁ ተናግረዋል፡፡ የሰሃላ ሰየምት ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሚሰው ፋናታየ በበኩላቸው የተከዜ ድልድይ በክረምት ወቅት በተደጋጋሚ ተመሳሳይ ችግሮች እንደሚያጋጥሙት አውስተዋል። በአሁኑ ወቅትም በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት ወንዙ መሙላቱን ተከትሎ ድልድዩ በደለል መዘጋቱ አስረድተዋል፡፡ በድልድዩ መዘጋትም ህብረተሰቡ የጤና፣ የንግድና ሌሎች አገልግሎቶችን ለማግኘት ወደ ሰቆጣና ጽጽቃ ከተሞች የሚደረገው ጉዞ በመቋረጡ ችግር መፍጠሩን አመልክተዋል። ከዞንና ከክልል ጋር በመነጋገር መፍትሄ እስኪመጣም በእናቶች ወሊድን እና ሌሎች ድንገተኛ አገልግሎቶችን በበለሳ ወረዳ እንዲያገኙ ለማድረግ እየተሰራ በመሆኑና ህብረተሰቡም ይህን አማራጭ እንዲጠቀም መልዕክት አስተላልፈዋል። የአማራ ክልል መንገድና ትራንስፖርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ አሰፋ ሲሳይ ድልድዩ ሲገነባ ከፍታው አጭር በመሆኑ የተከዜ ወንዝ ውሃ ሲሞላ ወደላይ ወጥቶ በየዓመቱ ስለሚያሰናክለው ቀድመው ከሶስት ወራት በፊት ለማስተካከል ጥረት መደረጉን ተናግረዋል። ይህም ሆኖ ችግሩ አሁንም በመፈጠሩ ጊዜያዊና ዘላቂ መፍትሄ ለማበጀት ከኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ጋር ተነጋገረው በጋራ ለመስራት ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ገልጸዋል      
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም