አርሶ አደሮች መሬትን ከአሲዳማነት በመከላከል ውጤታማ እየሆኑ ነው

243
ሀምሌ 27/2011 በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋና በምስራቅ ወለጋ ዞኖች አርሶ አደሮች መሬትን ከአሲዳማነት በመከላከል ጥሩ ውጤት እያገኙ መሆኑን ገለጹ። በክልሉ ምዕራብ ሸዋና በምስራቅ ወለጋ ዞኖች የሚገኙ አርሶ አደሮች መሬትን ከአሲዳማነት በመከላከል ጥሩ ውጤት እያገኙ መሆኑን ተናገሩ። አርሶ አደሮቹ ኖራንና የተሳቦ ቀልዝ ወይም በርሚ ኮምፖስት በመጠቀም የመሬትን አሲዳማነት በማካም ምርታቸውን በማሳደግ ላይ ናቸው። የተሳቦ ቀልዝ ማለት የአፈር ማዳበሪያን በትላትሎች አማካይነት ከእንስሳት እዳሪ የማምረት ቴክኖሎጂ ሲሆን ይህም ከአካባቢ ጋር ተስማሚ የሆነ የተፈጥሮ ማዳበሪያ ለማምረት ይረዳል። በመሆኑም በክልሉ ከ1 ነጥብ 9 ሚሊዮን ሄክታር መሬት በላይ በአሲዳማነት የተጠቃ ሲሆን ችገሩንም ለማስወገድ የተያዩ የመፍትሄ እርምጃዎች እየተሰዱ ይገኛል። ኢዜአ ያነጋገራቸው አርሶ አደሮች እንደሚሉትበ ከዚህ በፊት ምንም አይንት ምርት የማይበቅልበት መሬት አሁን ላይ ምርት ጀምሯል። ሆኖም የኖራ አቅርቦት እጥረት በመኖሩ በሚፈልጉት መጠን እያገኙ አለመሆኑን ጠቅሰዋል። በክልሉ የአፈር ለምነትና ማሻሻያ ደይሬክተር አቶ ኤሊያስ ከድር እንዳሉት የአፍር አሲዳማነትን ችግር ለማስወገደ የተለያዩ የመፍትሄ እርምጃዎች በመወሰድ ላይ መሆኑን አስረድተዋል። የኖራን በመጠቀም አፈር ማካም እና በስፋት ለመጠቀም እንዲያስችል በጉደር የሚገኘውን የኖራ ፋብሪካ ምርት አቅም ለማሳደግ ማስፋፊያ ስራ እየተካሄደ ይገኛልም ብለዋል። በቀጣይ አርሶ አደሩ ኖራን በግዥም ሆነ በብድር ማግኘት በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ እየተመቻቹ መሆኑንም እንዲሁ። የተሳቦ ቀልዝ ወይም በርሚ ካልቸርና በርሚ ኮምፖስት ማዕከላት ተገንብተው የማባዛት ስራዎች እየተከናወኑ ሲሆን የተፈጥሮ ማዳበሪያም በስፋት ጥቅም ላይ እየዋለ ነው ብለዋል። አሁን ያለው የኖራ ችግር ሳይሆን በቂ ማሺኖች ባለመኖራቸው መሆኑን ጠቅሰው በቀጣይ ማሺኖችን በብዛት በማምጣት እና በመትከል ችግሩ በዘላቂነት ይፈታል ብለዋል። በጉደር በ84 ሄክታር መሬት ላይ ያለውን የኖራ ድንጋይ በማውጣት የማምረት አቅምን ላማደግ ይሰራልም ብለዋል። የግብርና ኖራ አንድ ጊዜ መሬት ላይ በመጠቀም እስከ አምስት ዓመት ድረስ ከተጨማሪ ኖራ ውጪ መጠቀም እንደሚያስችል ገልጸዋል። የክልሉ ግብርና ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ እንዳልካቸው ተፈሪ እንዳሉት በክልሉ በዚህ ዓመት ከ58 ሺህ ኩንታል በላይ ኖራ አሲዳማነትን ለማከም ስራ ላይ ውሏል። በቀጣይም በእጥፍ ለመጨመር እየተሰራ መሆኑን አስረድተዋል። እንደ ሃላፊው ገለፃ 1 ነጥብ 9 ሚሊዮን ሄክታር መሬት በኖራ በአንድ ዓመት ለመሸፈን 445 ሚሊዮን ኩንታል የሚጠይቅ በመሆኑ ሌለሎች አማራጮችን በመጠቀም ላይ ይገኛሉ። እንደ መፍትሄ የኖራ ፋብሪካዎችን አቅም ከማሳደግ በተጨማሪ አሲዲቲን መቋቋም የሚችሉ ሰብሎችን መጠቀም ተጀምሯልም ብለዋል።    
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም