ሠራተኞች ደም ለገሱ

103
ጋምቤላ ሐምሌ 27/2011  የጋምቤላ ክልል ወሳኝ ኩነቶች ኤጀንሲ ሠራተኞች በወሊድና በአደጋ ወቅት በደም መፍሰስ የሚሞቱ እናቶችንና ህሙማንን ለመታደግ የደም ልገሳ መርሐ ግብር አካሄዱ። የኤጀንሲውን ሁለተኛ ዓመት ክብር በዓል በማስመልከት በተካሄደው መርሐ ግብር 85  ዩኒት ደም እንደተሰበሰበም ተገልጿል። የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰናይ አኩዎር በመርሐ ግብሩ ላይ እንዳሉት ኤጀንሲው ለሁለት ወራት የሚቆይ የበጎ ፈቃድ አገልገሎትና የኩነት ምዝገባ ስራዎችን በዘመቻ እያከናወነ ነው። በኤጀንሲው እየተከናወኑ ከሚገኙት የበጎ ፈቃድና የኩነት ምዝገባ ሥራዎች መካከል የደም ልገሳ፣ የችግኝ ተከላ፣ የተማሪዎች የልደት ምዝገባ እንደሚገኙበት ገልጸዋል። በዓሉን ምክንያት በማድረግ ሠራተኞቹ ባካሄዱት የደም ልገሳ  85 ዩኒት ደም መሰብሰቡንና ከስድስት ሺህ በላይ ችግኞች መተከላቸውን ተናግረዋል። በቀጣይም በጋምቤላ ከተማ ከ23 ሺህ የሚበልጡ ተማሪዋችን በመመዝገብ የልደት ምስክር ወረቀት ለመስጠት እየተሰራ መሆኑንም ዋና ዳይሬክተሩ አስታውቀዋል። በተጨማሪም የወሳኝ ኩነት ምዝገባ  በዘመናዊ የመረጃ አያያዝ ያለውን ጠቀሜታ የሚያስገነዝቡ ዐውደ ጥናቶች ይካሄዳሉ ብለዋል። በደም ልገሳው ከተሳተፉት ሰራተኞች መካከል አቶ እስክንድር ሱሌማን በሰጡት በደም መፍሳስ ምክንያት የሚሞቱ እናቶችንና ሕፃናትን ለመታደግ  ደማቸውን መለገሳቸውን ተናግረዋል። በወሊድና በአደጋ ወቅት በደም መፍሳስ ምክያት የሚጎዱትን ዜጎች ለመታደግ የተጀሩትን የደም ልገሳውን በሌላም ጊዜ እንደሚያደርጉ የተናገሩት ደግሞ አቶ ባጉየል ጆክ ናቸው። የወገን ደራሽ ለወገን ማህበር ተጠሪ አቶ ዘሪሁን በየነ በሰጡት አስተያየት ኤጀንሲው ባዘጋጀው መርሸ ግበር ስምንት አባላት ደም መለገሳቸውን ተናግረዋል ። በቀጣይም ማህበሩ ተመሳሳይ መረሕግብር በማዘጋጅት ከ300በላይ የማህበሩ አባላት ደም ለመለገዝ እቅድ መያቸውን ገልጸዋል። የጋምቤላ ክልል ደም ባንክ ማዕከል አስተባባሪ አቶ ኡጁሉ ኡዶላ በዚሁ ጊዜ እንዳሉት የኤጀንሲው ሠራተኞች በራሳቸው ተነሳሽነት በአጭር ጊዜ ውስጥ ባደረጉት ንቅናቄ  በወር የሚሰበሰበውን ደም በአንድ ጊዜ  ለመሰብሰብ እንዳስቻሉት ተናግረዋል። መሆኑም በደም መፍሰስ ምክንያት የሚሞቱ እናቶችና ሌሎች ሕሙማን ለመታደግ በኤጀንሲው የተጀመረው መልካም ተግባር በሌሎችም ተቋማት እንዲጠናከር ጠይቀዋል። በክልሉ ወሳኝ ኩነቶች ሐምሌ 10 ቀን 2011 የተጀመረው የበጎ ፈቃድና የኩነቶች ምዘገባ ዘመቻ ነሐሴ 30 ቀን 2011 ይጠናቀቃል።  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም