በህገ ወጥ መንገድ 110 ሺህ ዶላር ሲያጓጉዝ የተገኘ ግለሰብ ተያዘ

254

ሀምሌ17/2011 በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ጠገዴ ወረዳ አንድ ግለሰብ በህግ ወጥ መንገድ 110ሺህ የአሜሪካ ዶላር በእጅ ሻንጣ ድብቆ ሲያጓጉዝ ተደርሶበት መያዙን ፖሊስ አስታወቀ።

ከዶላሩበተጨማሪአንድባለ 20 የእንግሊዝፓውንድአብሮተይዟል፡፡

በዞኑ ፖሊስ መምሪያ የወንጀል መከላከል የስራ ሂደት አስተባባሪ ምክትል ኮማንደር አስማማው ካሳ ዛሬ ለጋዜጠኞች እንደገለጹት ግለሰቡ ከነዶላሩ የተያዘው ባለፈው እሁድ ከቀኑ ሰዓት አካባቢ በወረዳው ሰሮቃ በተባለው የፍተሻ ኬላ ላይ ነው፡፡

ግለሰቡሊያዝየቻለውከመኪናወርዶኬላውንበእግርለማለፍሲሞክርነው፡፡

በወቅቱበኬላውየተመደቡየፖሊስናሌሎችየጽጥታአካላትግለሰቡንበጥርጣሬይዘውፍተሻሲያደርጉበእጅሻንጣውውስጥበረቀቀመንገድበተዘጋጀስፍራዶላሩንደብቆመገኘቱንምክትልኮማንደርአስማማውተናግሯዋል፡፡

ግለሰቡ መንጃ ፈቃድ ለማውጣት ዶላሩን እንደያዘው መናገሩን ጠቅሰው ከጎንደር ከተማ ወደ ሁመራ ሲጓዝ እንደነበርም አስረድተዋል፡፡

ምክትል ኮማንደሩ እንዳሉ ግለሰብ በአሁኑ ወቅት በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውሎ በተቋቋመው የወንጀል መርማሪ ቡድን ድርጊቱ በመጣራት ላይ ነው፡፡

በቁጥጥር ስር የዋለው ዶላር በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጎንደር ዲስትሪክት ትክክለኛነቱ ተረጋግጧል ።

ከዶላሩበተጨማሪአንድባለ 20 የእንግሊዝፓውንድአብሮመያዙምተገልጿል፡፡

ህገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር ሀገር የሚጎዳ በመሆኑ ህብረተሰቡ አዘዋዋሪዎችን በመጠቆም ትብብሩን አጠናክሮ እንዲቀጥል ምክትል ኮማንደሩ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡