ካሜሩን በማረሚያ ቤት ለተቀሰቀሰው አመፅ ተቃዋሚ ፓርቲን ወቀሰች

120

ሐምሌ 17/2011 የካሜሮን መንግስት  በዋና ከተማዋ በሚገኘው ማረሚያ ቤት የተቀሰቀሰው አመፅ በማረሚያ ቤቱ ውስጥ ባሉ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራር ደጋፊዎች ነው የሚል ወቀሳ አቅርቧል።

ቢቢሲ እንደዘገበው  ባለፈው እሁድ ማታ በማረሚያ ቤቱ ችግሩ ሲቀሰቀስ የማረሚያ ቤቱ ጥበቃ እንዳለው፤ የቡድን ረብሻ፣የማረሚያ ቤቱ ላይብራሪና ክሊኒክ ቃጠሎ እንዲሁም የሴት ታራሚዎች የመስሪያ ቦታ ሲያወድሙ ተመልክቷል፡፡

የመንግስት ከፍተኛ አመራር የሆኑት ጄን ክላውድ ቲላ የጉዳቱን መጠን ለመመልከት ወደ ማረምያ ቤቱ ባቀኑበት ወቅት እንደገለፁት፤ አመፁ CRM በተሰኘ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ካምቶስ ደጋፊዎች አነሳሽነት ነው የተቀሰቀሰው፡፡

ቢያንስ 400 የሚሆኑ ደጋፊዎቻቸው በከተማዋ በተለያዩ ተቋማት በመስራት ላይ እንደሚገኙና በማረሚያ ቤት በአመፅ ቀስቃሽነት የተሳተፉ ቁጥራቸው በግልፅ እንዳተጠቀሰ  ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

የተቃዋሚ ፓርቲ ደጋፊዎቹ በቁጥጥር ስር ከዋሉበት ጀምሮ በካሜሮን አመፅ  ተበራክቷል ያሉት ሃላፊው “አማፅያኖቹ በደጋፊዎቻቸው ጀርባ በመደበቅ በአገሪቷ ሰላምና መረጋጋት እንዳይኖር በመስራት ላይ እንደሆኑ እናውቃለን”  ነው ያሉት